እንደወደድከኝ ፡ አወኩ (Endewededkegn Aweku) - ቤተልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)

Bethlehem Wolde 3.png


(3)

ቃልህን ፡ ወደድኩት
(Qalehen Wededkut)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 8:31
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

ምሥጋናን ፡ የሚሰዋ ፡ ያከብረኛል ፡ ያከብረኛል ፡ ብለሃል
እሰዋለሁ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ይኸው
እሰዋለሁ ፡ አምልኮዬ ፡ ይኸው (፪x)

ምሥጋናን ፡ በአፌ ፡ የጨመርክ
ምሬትን ፡ ከእኔ ፡ ያስወገድክ
አምላኬ ፡ አንተ ፡ ነህና
ይብዛልህ ፡ ዛሬም ፡ ምሥጋና
ይገባሃልና ፡ አሜን ፡ ይገባሃልና

እናመልክሃለን ፤ እናመልክሃለን
ከዙፋንህ ፡ ስርም ፡ እንሰግድልሃለን
እናመልክሃለን ፤ እናመልክሃለን
በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ እንሰግድልሃለን

ክብርህን ፡ ላውራ ፡ ጌታዬ
ሞገስ ፡ ያግኝ ፡ ምሥጋናዬ
ሳከብርህ ፡ ሁሌ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
እረካለሁ ፡ ክብርህ ፡ ያጠግበኛል
ክብርህ ፡ ያጠግበኛል ፡ አሜን ፡ ክብርህ ፡ ያጠግበኛል

እናመልክሃለን ፤ እናመልክሃለን
ከዙፋንህ ፡ ስርም ፡ እንሰግድልሃለን
እናመልክሃለን ፤ እናመልክሃለን
በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ እንሰግድልሃለን

ድል ፡ በመንሳቱ ፡ ለሚያዞረኝ
በጠላቶቼ ፡ ዕራስ ፡ ላይ ፡ ላቆመኝ
እዘምራለሁ ፡ ለጌታ ፡ እዘምራለሁ ፡ አሃ
እዘምራለሁ ፡ ለአምላኬ ፡ እዘምራለሁ ፡ ኦሆ

ያስጨናቂውን ፡ ዘንድ ፡ ጌታዬ ፡ ሰባበርከው
ግዙፉን ፡ ቀንበሬን ፡ ከላዬ ፡ አስወገድከው
ሁሌ ፡ እደነቃለሁ ፡ ጌታዬ ፡ በማዳንህ
ባለህ ፡ ምሥጋና ፡ ላይ ፡ ሌላም ፡ ልጨምርልህ (፪x)

ዝናህን ፡ አወራለሁ (፫x) ፡ ማዳንህን ፡ እናገራለሁ
ዝናህን ፡ አወራለሁ (፫x) ፡ ማዳንህን ፡ እናገራለሁ

ጣላቴ ፡ ይዞራል ፡ የሚውጠው ፡ ፈልጐ
ምንም ፡ ላይሞላለት ፡ ሁሌ ፡ መናውን ፡ ቀርቶ
እኔን ፡ ግን ፡ ጌታዬ ፡ ከድል ፡ ድል ፡ ያዞረኛል
ጠላቴን ፡ ከእግሬ ፡ ስር ፡ ጌታዬ ፡ አስረግጦኛል (፪x)

ጠላቴ ፡ ዕልል ፡ አይልብኝምና
እንደወደድከኝ ፡ አወቅሁ
እንደመረጥከኝ ፡ አወቅሁ (፪x)

በእኔ ፡ ድንኳን ፡ ዕልልታ ፡ ይሰማዋል ፡ ዝማሬ ፡ ይሰማዋል
የወደደኝ ፡ ጌታ ፡ ይህንን ፡ አድርጓል
የመረጠኝ ፡ እርሱ ፡ ይህንን ፡ አድርጓል

የማንም ፡ ባለዕዳ ፡ ያልሆነው ፡ እግዚአብሔር
አፈራረሰና ፡ የጠላቶቼን ፡ ምክር
አዳዲስ ፡ ዝማሬ ፡ በአፌ ፡ ውስጥ ፡ ሲጨምር
የነፍሴ ፡ ቅኝቷ ፡ ሁሌ ፡ ክብር ፡ ክብር (፪x)

ዝናህን ፡ አወራለሁ (፫x) ፡ ማዳንህን ፡ እናገራለሁ
ዝናህን ፡ አወራለሁ (፫x) ፡ ማዳንህን ፡ እናገራለሁ

ክበር ፡ ከሚሉህ ፡ ጋር ፤ ንገሥ ፡ ከሚሉህ ፡ ጋር (፪x)
እስማማለሁ ፡ እኔም ፡ እጨምራለሁ (፬x)
ክበር ፡ ከሚሉህ ፡ ጋር ፤ ንገሥ ፡ ከሚሉህ ፡ ጋር (፪x)
እስማማለሁ ፡ እኔም ፡ እጨምራለሁ (፬x)