ደርቤ (Derebie) - ቤተልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)

Bethlehem Wolde 3.png


(3)

ቃልህን ፡ ወደድኩት
(Qalehen Wededkut)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:03
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

ደርቤ ፡ ደርቤ ፡ ላብዛው ፡ ምሥጋናዬን
ለምወደውና ፡ ለቸሩ ፡ ጌታዬ
ምሥጋና ፡ ይብዛልህ ፡ አሃሃ
አምልኮና ፡ ክብር ፡ ኦሆሆ
ይሄ ፡ ነው ፡ መሻቴ ፡ አሃሃ
አንተን ፡ እንዳስከብር ፡ ኦሆሆ

አዝ፦ የልቤ ፡ ናፍቆት ፡ ስትከብር ፡ ማየት ፡ ነው
አቤቱ ፡ አመሰግንሃለሁ (፬x)

በሕይወቴ ፡ ብርሃን ፡ ብርሃን ፡ ይሁን ፡ ያልከው
እግዚአብሔር ፡ ተባረክ ፡ በሰማይ ፡ ያለኸው
ከክብር ፡ ጋር ፡ ጌታ ፡ አሃሃ
ተቀብለኸኛል ፡ ኦሆሆ
ከፊትህ ፡ ጋር ፡ ደስታን ፡ ኣሃሃ
አንተ ፡ አጥግበኸኛል ፡ ኦሆሆ

አዝ፦ የልቤ ፡ ናፍቆት ፡ ስትከብር ፡ ማየት ፡ ነው
አቤቱ ፡ አመሰግንሃለሁ (፬x)

ከጠላት ፡ መንጋጋ ፡ ያወጣኝ ፡ ፈልቅቆ
የምኖርበትን ፡ አይቶታል ፡ አርቆ
የክብሩ ፡ ፀዳል ፡ አሃሃ
በእኔ ፡ ላይ ፡ በራልኝ ፡ ኦሆሆ
ያስጨነቀኝ ፡ ሁሉ ፡ አሃሃ
በረከት ፡ ሆነልኝ ፡ ኦሆሆ

አዝ፦ የልቤ ፡ ናፍቆት ፡ ስትከብር ፡ ማየት ፡ ነው
አቤቱ ፡ አመሰግንሃለሁ (፬x)
የልቤ ፡ ናፍቆት ፡ ስትከብር ፡ ማየት ፡ ነው
አቤቱ ፡ አመሰግንሃለሁ (፬x)