በሌሊትም (Belielitem) - ቤተልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)

Bethlehem Wolde 3.png


(3)

ቃልህን ፡ ወደድኩት
(Qalehen Wededkut)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 5:11
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

በሌሊትም ፡ ከልቤ ፡ ጋር ፡ ተጫወትኩኝ
ነፍሴንም ፡ አነቃቃኋት ፡ ጌታን ፡ አሰብኩኝ
እርሱን ፡ ሳስብ ፡ ልቤ ፡ በደስታ ፡ ሁሌ ፡ ይሞላል
ያስጨነቀኝንም ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ይጥላል

እግዚአብሔርን ፡ ሳየው ፡ ደስ ፡ አለኝ
እግዚአብሔርን ፡ አሰብኩት ፡ ደስ ፡ አለኝ
እርሱን ፡ ተመልከቱ ፡ ያበራላችኋል (፪x)
የጨለመውንም ፡ ጌታ ፡ ይገፈዋል (፪x)
ወደ ፡ እርሱ ፡ ቅረቡ ፡ ያበራላችኋል
የጨለመውን ፡ ጌታ ፡ ይገፈዋል (፪x)

ለተጨነቀ ፡ ሰው ፡ ጨለማ ፡ አይሆንም ፡ ብሏል
በእውነት ፡ ለሚታመኑት ፡ ልቡ ፡ ይራራል
አሁንም ፡ ተስፋዬም ፡ ትዕግሥቴም ፡ በእርሱ ፡ ነው
በዘመኔ ፡ እያሰብኩት ፡ እደሰታለሁ

እግዚአብሔርን ፡ ሳየው ፡ ደስ ፡ አለኝ
እግዚአብሔርን ፡ አሰብኩት ፡ ደስ ፡ አለኝ
እርሱን ፡ ተመልከቱ ፡ ያበራላችኋል (፪x)
የጨለመውንም ፡ ጌታ ፡ ይገፈዋል (፪x)
ወደ ፡ እርሱ ፡ ቅረቡ ፡ ያበራላችኋል
የጨለመውን ፡ ጌታ ፡ ይገፈዋል (፪x)

ስትፈለግ ፡ የምትገኝ ፡ አንተ ፡ ነህ
ምታጽናና ፡ ምትደግፍ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ
በብርሃንህ ፡ ብርሃን ፡ እንዳይ ፡ አደረከኝ
በቀረብኩህ ፡ ቁጥር ፡ ጌታ ፡ አበራህልኝ

አንተ ፡ ሙሉ ፡ ነህ ፡ እታመንሃለሁ
ዓይኔን ፡ ከሰው ፡ ላይ ፡ ይኸው ፡ አንስቻለሁ
አንተ ፡ ብቻህን ፡ በቂ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ብቻህን (፪x)
አንተ ፡ ብቻህን ፡ ሙሉ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ብቻህን (፪x)

አንተ ፡ ሙሉ ፡ ነህ ፡ እታመንሃለሁ
ዓይኔን ፡ ከሰው ፡ ላይ ፡ ይኸው ፡ አንስቻለሁ
አንተ ፡ ብቻህን ፡ በቂ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ብቻህን (፪x)
አንተ ፡ ብቻህን ፡ ሙሉ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ብቻህን (፪x)