የከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ነው (Yekentu Kentu New) - ቤቴልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤቴልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)

Lyrics.jpg


(2)

ቸር ፡ ነህ
(Cher Neh)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤቴልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

አዝ:- አይን ፡ ከማየት ፡ አይጠግብም
ጆሮም ፡ ከመስማት ፡ አይሞላም
በአለም ፡ ያለው ፡ ከንቱ ፡ ነው
የከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ንፋስን ፡ እንደመከተል ፡ ነው
(፪x)
እግዚአብሄር ፡ ሆይ ፡ በዘመኔ ፡ ይህን ፡ እሻለሁ
ክብርህን ፡ ሳይ ፡ ብቻ ፡ እጠግባለሁ (፪x)
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ በዘመኔ ፡ ይህ ፡ እሻለሁ
ክብርህን ፡ ሳይ ፡ ብቻ ፡ እጠግባለሁ (፪x)

ሁሉን ፡ አየሁ ፡ ተመለከትኩ
ከአንተ ፡ ሌላ ፡ እርካታ ፡ እንደሌለ ፡ አወቅኩ
ሁሉም ፡ ከንቱ ፡ እጅግ ፡ ከንቱ ፡ ነው
አንተን ፡ ማግኘት ፡ ጌታ ፡ የጥበብ ፡ ጥበብ ፡ ነው

አዝ:- አይን ፡ ከማየት ፡ አይጠግብም
ጆሮም ፡ ከመስማት ፡ አይሞላም
በአለም ፡ ያለው ፡ ከንቱ ፡ ነው
የከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ንፋስን ፡ እንደመከተል ፡ ነው
(፪x)
እግዚአብሄር ፡ ሆይ ፡ በዘመኔ ፡ ይህን ፡ እሻለሁ
ክብርህን ፡ ሳይ ፡ ብቻ ፡ እጠግባለሁ (፪x)
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ በዘመኔ ፡ ይህ ፡ እሻለሁ
ክብርህን ፡ ሳይ ፡ ብቻ ፡ እጠግባለሁ (፪x)

ሃብትም ፡ ንብረት ፡ አላፊ ፡ ነው
ውበትም ፡ ደም ፡ ግባት ፡ ቁንጅና ፡ ጠፊ ፡ ነው
ከሁሉም ፡ በላይ ፡ የምታስመካ
አንተ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ የዘላለም ፡ ተስፋ

አዝ:- አይን ፡ ከማየት ፡ አይጠግብም
ጆሮም ፡ ከመስማት ፡ አይሞላም
በአለም ፡ ያለው ፡ ከንቱ ፡ ነው
የከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ንፋስን ፡ እንደመከተል ፡ ነው
(፪x)
እግዚአብሄር ፡ ሆይ ፡ በዘመኔ ፡ ይህን ፡ እሻለሁ
ክብርህን ፡ ሳይ ፡ ብቻ ፡ እጠግባለሁ (፪x)
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ በዘመኔ ፡ ይህ ፡ እሻለሁ
ክብርህን ፡ ሳይ ፡ ብቻ ፡ እጠግባለሁ (፪x)

ትውልድ ፡ ሄዶ ፡ ትውልድ ፡ ይመጣል
ጸንቶ ፡ ሚኖር ፡ የለም ፡ ሁሉም ፡ ይለወጣል
የማይለወጥ ፡ ፍጹም ፡ የሆነ
አምላኬ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ሁሌ ፡ የታመነ

አዝ:- አይን ፡ ከማየት ፡ አይጠግብም
ጆሮም ፡ ከመስማት ፡ አይሞላም
በአለም ፡ ያለው ፡ ከንቱ ፡ ነው
የከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ነው
ንፋስን ፡ እንደመከተል ፡ ነው
(፪x)