ታምራትን (Tameraten) - ቤቴልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤቴልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)

Lyrics.jpg


(2)

ቸር ፡ ነህ
(Cher Neh)

ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤቴልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

ብቻህን ፡ ታምራትን ፡ አንተ ፡ ትሰራለህ
የማመልክህ ፡ እግዚአብሄር ፡ አንተ ፡ ሁሉንም ፡ ቻይ ፡ ነህ (፪x)

ደመና ፡ ሳታሳይ ፡ ዝናብ ፡ ታዘንባለህ
ከደረቀው ፡ አለት ፡ ውሃ ፡ ታፈልቃለህ
በቃልህ ፡ ስታዝዘው ፡ ሁሉ ፡ ይታዘዝሃል
የፍጥረት ፡ ገዢ ፡ ነህ ፡ ማንስ ፡ ይመስልሃል

ብቻህን ፡ ታምራትን ፡ አንተ ፡ ትሰራለህ
የማመልክህ ፡ እግዚአብሄር ፡ አንተ ፡ ሁሉንም ፡ ቻይ ፡ ነህ (፪x)

ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ለኔ ፡ እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነህ
ለሰው ፡ ሁሉ ፡ ወዳጅ ፡ ሁሉ ፡ የተቻለህ
እኔም ፡ ባንተ ፡ ጌታ ፡ እተማመናለሁ
ሞትንም ፡ ወስደሃል ፡ እኮራብሃለሁ

ብቻህን ፡ ታምራትን ፡ አንተ ፡ ትሰራለህ
የማመልክህ ፡ እግዚአብሄር ፡ አንተ ፡ ሁሉንም ፡ ቻይ ፡ ነህ (፪x)

ማንም ፡ ሳያቅትህ ፡ ማንም ፡ ሳይመክርህ
ዓለምን ፡ ሞላዋን ፡ አንተ ፡ መሠረት
ወብና ፡ ድንቅ ፡ አርገህ ፡ እኛን ፡ ፈጥረኸናል
የእጆችህ ፡ ስራዎች ፡ አመስግነንሃል

በተስፋ ፡ ለሚጠብቁት ፡ ለምትሻውም ፡ ነፍስ
ጌታ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ይሰጣል ፡ እረፍት
እርሱን ፡ ታምኖ ፡ ጠብቆ ፡ ያፈረ ፡ ማነው
ጸሎቴን ፡ ሰምቷል ፡ ጌታን ፡ ላክብረው

ዛሬም ፡ ላሞጋግስህ ፡ ክበርልኝ ፡ ክበርልኝ
ውለታህን ፡ ልቁጠረው ፡ ንገሥልኝ ፡ ንገሥልኝ
ጸሎቴን ፡ ሰምተሃል ፡ ክበርልኝ ፡ ክበርልኝ
ጠላቴን ፡ ረግጠሃል ፡ ንገሥልኝ ፡ ንገሥልኝ

ከፍ ፡ በል ፡ ዝማሬ ፡ ይድረስህ
ሌላማ ፡ የለኝም ፡ የምሰጥህ (፪x)

ጌታን ፡ የሚጠብቁ ፡ ቅዱሳን ፡ ሁሉ
ከመልካም ፡ ነገር ፡ አንዳች ፡ አይጐድሉ
እኔም ፡ በዘመኔ ፡ ተጠግቼዋለሁ
ከመልካም ፡ ነገር ፡ ሁሌ ፡ እጠግባለሁ

ዛሬም ፡ ላሞጋግስህ ፡ ክበርልኝ ፡ ክበርልኝ
ውለታህን ፡ ልቁጠረው ፡ ንገሥልኝ ፡ ንገሥልኝ
ጸሎቴን ፡ ሰምተሃል ፡ ክበርልኝ ፡ ክበርልኝ
ጠላቴን ፡ ረግጠሃል ፡ ንገሥልኝ ፡ ንገሥልኝ