ስላንተማ (Selantema) - ቤቴልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤቴልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)

Lyrics.jpg


(2)

ቸር ፡ ነህ
(Cher Neh)

ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤቴልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

አዝ:- ስላንተማ ፡ ብዙ ፡ ምናገረው ፡ አለኝ (፪x)
የትኛውን ፡ አንስቼ ፡ የትኛውን ፡ እተዋለሁ
ጌታዬ ፡ ስራህ ፡ እኮ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)

እግዚአብሄር ፡ ኃያል ፡ ነህ ፡ ማንንም ፡ አትንቅም
ደካማን ፡ በመጣል ፡ አንተ ፡ አትታወቅም
ከጥንት ፡ የሰማነው ፡ በዓይናችን ፡ ያየነው
ጻድቅነትና ፡ ሰውን ፡ መውደድህ ፡ ነው (፪x)

አዝ:- ስላንተማ ፡ ብዙ ፡ ምናገረው ፡ አለኝ (፪x)
የትኛውን ፡ አንስቼ ፡ የትኛውን ፡ እተዋለሁ
ጌታዬ ፡ ስራህ ፡ እኮ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)

ጥንት ፡ አባቶቻችን ፡ ስራህን ፡ አወሩ
ድንቅ ፡ ታምራትህን ፡ እየመሰከሩ
ስራህ ፡ እግዚአብሄር ፡ ሆይ ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው
እኔ ፡ ምስክር ፡ ነኝ ፡ በዓይኔ ፡ አይቻለሁ (፪x)

አዝ:- ስላንተማ ፡ ብዙ ፡ ምናገረው ፡ አለኝ (፪x)
የትኛውን ፡ አንስቼ ፡ የትኛውን ፡ እተዋለሁ
ጌታዬ ፡ ስራህ ፡ እኮ ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው (፪x)

የማወራው ፡ አለኝ ፡ የምመሰክረው
ስለአንተ ፡ ምህረት ፡ ፍቅር ፡ የምናገረው
ሥለ ፡ ሰው ፡ ልጅ ፡ ሃጢአት ፡ ልጅህን ፡ ሰጥተሃል
በእውነተኛ ፡ ፍቅርህ ፡ እኛን ፡ አድነሃል (፪x)

ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ፍቅርህ
እኛን ፡ መውደድህ (፬x)

ክበር ፡ እንጂ ፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ እንላለን
በላይ ፡ በላይ ፡ ምስጋና ፡ እንጨምራለን
በላይ ፡ በላይ ፡ ክብር ፡ እንጨምራለን

ንገስ ፡ እንጂ ፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ እንላለን
በላይ ፡ በላይ ፡ ምስጋና ፡ እንጨምራለን
በላይ ፡ በላይ ፡ ዝማሬ ፡ እንጨምራለን

ልነሳና ፡ ልነሳና
ላክብርህ ፡ ምክንያት ፡ አለኝ
ብዙ ፡ ብዙ ፡ ምክንያት ፡ አለኝ ፡ ክበር (፫x)

ምስጋና ፡ ላንተ ፡ ነው ፣
ክብርም ፡ ላንተ ፡ ነው
አምልኮ ፡ ላንተ ፡ ነው ፣
ስግደትም ፡ ላንተ ፡ ነው

ያረክልን ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ጌታ (፪x)
ያረክልን ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ አሃሃሃ (፪x)

ውዳሴም ፡ ላንተ ፡ ነው ፣
ቅዳሴም ፡ ላንተ ፡ ነው
ጭብጨባም ፡ ላንተ ፡ ነው ፣
እልልታም ፡ ላንተ ፡ ነው

ያረክልን ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ጌታ (፪x)
ያረክልን ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ አሃሃሃ (፪x)