Bethlehem Wolde/Cher Neh/Menoriyayie

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ቤቴልሔም ወልዴ ርዕስ መኖሪያዬ አልበም ቸር ነህ

አዝ መኖሪያዬ ነህ ጌታዬ መኖሪያዬ ነህ ኢየሱስ (፪x) አሳርፈኸኛል እፎይ እፎይ ብያለሁ አንተን አግኝቻለሁ (፪x)

ወዳጅ እንደሌላቸው አልተዋችሁም አልረሳችሁም ብለህ ተናግረሃል ያልከውን ልትፈጽም አንተ ሄደሃል አንተ ባለህበት እኛን ልታኖረን ልታሳርፈን በቅርብ ትመጣለህ አሜን ጌታችን ቶሎ ናልን

አዝ መኖሪያዬ ነህ ጌታዬ መኖሪያዬ ነህ ኢየሱስ (፪x) አሳርፈኸኛል እፎይ እፎይ ብያለሁ አንተን አግኝቻለሁ (፪x)

በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ ማረፊያ አለ ተመለሱ ይብቃ ኑ ወደ እረፍቱ ግቡ ትላለህ ሰምቶ ላመነበት መኖሪያ አንተ ነህ ማረፊያ አንተ ነህ ነፍስን ከሚያጐድል ትጠብቃለህ ትጋርዳለህ

አዝ መኖሪያዬ ነህ ጌታዬ መኖሪያዬ ነህ ኢየሱስ (፪x) አሳርፈኸኛል እፎይ እፎይ ብያለሁ አንተን አግኝቻለሁ (፪x)

ምድር ብትነዋወጥ ብትነዋወጥ ሁሉም ነገር ስፍራውን ቢለቅ ከቶ እንዳልፈራ ከቶ እንዳልናወጥ ልቤን ሞላኸው በሰላም በእረፍት ያረጋጋኸኝ በነውጡ አለም ጋሻዬ ነህና ለዘለአለም እኔ ልበልህ እረድኤቴ ስለሆንክልኝ አቅም ጉልበቴ እልሀለሁ እረድኤቴ(6)