ክበር ፡ ትልሃለች (Keber Telehalech) - ቤቴልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤቴልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)

Lyrics.jpg


(2)

ቸር ፡ ነህ
(Cher Neh)

ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤቴልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

አዳኝ ፡ ነህ ፡ ከእስራት ፡ ምትፈታ
ለጠላጥህ ፡ የማትረታ
የኔን ፡ ነፍስ ፡ ከጠላት ፡ ተሟግተህ
አዳንካት ፡ ከእስራቷ ፡ ፈተህ

አዝ:- ያዳንካትም ፡ ነፍሴ ፡ ሁልጊዜ ፡ ሁሌ ፡ ሁልጊዜ
ክበር ፡ ትልሃለች ፡ ጌታ ፡ እየሱሴ
(፪x)
ክበር ፡ ክበርልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ክበር ፡ ክበርልኝ
ንገሥ ፡ ንገሥልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ንገሥ ፡ ንገሥልኝ

ከነኃጥያቴ ፡ ያኔ ፡ ወደድከኝ
ዘላለም ፡ ያንተው ፡ አደረከኝ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ በእውነት ፡ ፍቅር ፡ ነህ
እኔን ፡ የሚወድድ ፡ ልብ ፡ አለህ

አዝ:- ያዳንካትም ፡ ነፍሴ ፡ ሁልጊዜ ፡ ሁሌ ፡ ሁልጊዜ
ክበር ፡ ትልሃለች ፡ ጌታ ፡ እየሱሴ
(፪x)
ክበር ፡ ክበርልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ክበር ፡ ክበርልኝ
ንገሥ ፡ ንገሥልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ንገሥ ፡ ንገሥልኝ

የኔ ፡ ሩጫ ፡ ውጊያው ፡ ከንቱ ፡ ነው
ሰልፉ ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ አምናለሁ
ቆሜ ፡ ማዳንህን ፡ እያየሁ
ለነገም ፡ ተስፋ ፡ አደርግሃለሁ

አዝ:- ያዳንካትም ፡ ነፍሴ ፡ ሁልጊዜ ፡ ሁሌ ፡ ሁልጊዜ
ክበር ፡ ትልሃለች ፡ ጌታ ፡ እየሱሴ
(፪x)
ክበር ፡ ክበርልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ክበር ፡ ክበርልኝ
ንገሥ ፡ ንገሥልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ንገሥ ፡ ንገሥልኝ

ማዳኑ ፡ ለሚፈሩት ፡ ቅርብ ፡ ነው
ምህረቱ ፡ እስከልጅ ፡ ልጆች ፡ ነው
እኔም ፡ ሳላቋርጥ ፡ እጠራሃለሁ
ክብርህንም ፡ እንዳይ ፡ አምናለሁ

አዝ:- ያዳንካትም ፡ ነፍሴ ፡ ሁልጊዜ ፡ ሁሌ ፡ ሁልጊዜ
ክበር ፡ ትልሃለች ፡ ጌታ ፡ እየሱሴ
(፪x)
ክበር ፡ ክበርልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ክበር ፡ ክበርልኝ
ንገሥ ፡ ንገሥልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ንገሥ ፡ ንገሥልኝ

ከልብ ፡ የማይጠፋ ፡ ዉለታ ፡ አለብኝ
ጌታዬ ፡ ለኔ ፡ ያደረገልኝ
በእድሜ ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ እገዛለታለሁ
በቤቱም ፡ ሁሌ ፡ አዘማለሁ

ተመስገን ፡ እለዋለሁ
ከእግሩ ፡ ስር ፡ አሰግዳለሁ (፪x)

ምስጋናዬ ፡ ይብዛልህ ፡ ክበርልኝ
ዛሬም ፡ አይነስብህ ፡ ይድረስልህ (ሃሌሉያ)
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ የምሰጠው
ጠዋት ፡ ማታ ፡ ወዳንተ ፡ ማሳርገው

ክበር ፡ ክበርልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ክበር ፡ ክበርልኝ
ንገሥ ፡ ንገሥልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ንገሥ ፡ ንገሥልኝ

በስራህ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ በስራህ
በአዲስ ፡ ዝማሬ ፡ በአፌ ፡ የጨመርህ
ልቤን ፡ በደስታ ፡ ስለሞላኸው
ሁሌ ፡ ለአንተ ፡ እንድዘምር ፡ ነው

ተመስገን ፡ እልሃለሁ
ከእግሩ ፡ ስር ፡ አሰግዳለሁ (፪x)

ምስጋናዬ ፡ ይብዛልህ ፡ ክበርልኝ
ዛሬም ፡ አይነስብህ ፡ ይድረስልህ (ሃሌሉያ)
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ለአንተ ፡ የምሰጠው
ጠዋት ፡ ማታ ፡ ወዳንተ ፡ ማሳርገው

ክበር ፡ ክበርልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ክበር ፡ ክበርልኝ
ንገሥ ፡ ንገሥልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ንገሥ ፡ ንገሥልኝ