ግዛኝ (Gezagn) - ቤቴልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤቴልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)

Lyrics.jpg


(2)

ቸር ፡ ነህ
(Cher Neh)

ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤቴልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

እኔስ ፡ እግዚአብሄር ፡ ሆይ ፡ በአንተ ፡ እምካለሁ
በክንፎችህ ፡ ጥላ ፡ ሁልጊዜ ፡ አርፋለሁ
በኔ ፡ ላይ ፡ የተሾምክ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ጌታ
እገዛልሃለሁ ፡ ዛሬም ፡ በደስታ፣ዛሬም ፡ በደስታ (፪x)

አዝ፦ግዛኝ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፣ ግዛኝ ፡ እገዛለሁ
ግዛኝ ፡ በሕይወቴ ፡ ላይ ፣ ግዛኝ ፡ ሾሜሃለሁ
ግዛኝ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፣ግ ዛኝ ፡ እገዛለሁ
ግዛኝ ፡ በልቤ ፡ ላይ ፣ ግዛኝ ፡ ሾሜሃለሁ

አስፈራርተህ ፡ አይደል ፡ እኔን ፡ የጠራኀኝ
በቀራንዮ ፡ ፍቅርህ ፡ ስበህ ፡ እየማረከኝ
እስከሽምግልና ፡ ልትሸከመኝ
የወደድከኝ ፡ ጌታ ፡ ለዘላለም ፡ ግዛኝ ፣ ለዘላለም ፡ ግዛኝ (፪x)

አዝ፦ግዛኝ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፣ ግዛኝ ፡ እገዛለሁ
ግዛኝ ፡ በሕይወቴ ፡ ላይ ፣ ግዛኝ ፡ ሾሜሃለሁ
ግዛኝ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፣ግ ዛኝ ፡ እገዛለሁ
ግዛኝ ፡ በልቤ ፡ ላይ ፣ ግዛኝ ፡ ሾሜሃለሁ

ወደኸኛል ፡ ጌታ ፡ እኔም ፡ ወድጄሃለሁ
የዘላለም ፡ ምርጫ ፡ አንተን ፡ አድርጌያለሁ
የአንተ ፡ በመሆኔ ፡ በጣም ፡ ረክቻለሁ
እጆቼን ፡ አንስቼ ፡ ግዛኝ ፡ እልሃለሁ ፣ ግዛኝ ፡ እልሃለሁ (፪x)

አዝ፦ግዛኝ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፣ ግዛኝ ፡ እገዛለሁ
ግዛኝ ፡ በሕይወቴ ፡ ላይ ፣ ግዛኝ ፡ ሾሜሃለሁ
ግዛኝ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፣ግ ዛኝ ፡ እገዛለሁ
ግዛኝ ፡ በልቤ ፡ ላይ ፣ ግዛኝ ፡ ሾሜሃለሁ