Bethlehem Wolde/Cher Neh/Cher Neh

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በቀራንዮ መስቀል ላይ
ስራዬን አንተ ሰርተሃል
ቀንበሬን አንተ ሰበርከው
እዳዬን ከኔ አስወገድከው (፪)

ቸር ነህ ለኔ ቸር ነህ (፪x)
ቸር ነህ ጌታዬ ቸር ነህ
ቸር ነህ ለኔ ቸር ነህ

ለኔ እንዳንተ ማን አለኝ
የውስጤ ልቤን የሚረዳልኝ
ስለኔ ሁሌ ታስባለህ
በአብ ዘንድ ትማልዳለህ

ብዙ ብዙ ነው ቸርነትህ ብዙ ነው
ብዙ ብዙ ነው በጐነትህ ብዙ ነው
ብዙ ብዙ ነው ምህረትህ ብዙ ነው
ብዙ ብዙ ነው ይቅርታህ ብዙ ነው

በደሙ አጥቦ አንጽቶ
ሕይወቴንም ለውጦ
ሰው አደረገኝ ረድኤቴ
እኔም ላክብረው ከልቤ (፪x)

ቸር ነህ ለኔ ቸር ነህ
ቸር ነህ ለኔ ቸር ነህ
ቸር ነህ ጌታዬ ቸር ነህ
ቸር ነህ ለኔ ቸር ነህ

ብዙ ብዙ ነው ቸርነትህ ብዙ ነው
ብዙ ብዙ ነው በጐነትህ ብዙ ነው
ብዙ ብዙ ነው ምህረትህ ብዙ ነው
ብዙ ብዙ ነው ይቅርታህም ብዙ ነው(፪)