በከፍታ (Bekefta) - ቤቴልሔም ፡ ወልዴ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤቴልሔም ፡ ወልዴ
(Bethlehem Wolde)

Lyrics.jpg


(2)

ቸር ፡ ነህ
(Cher Neh)

ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤቴልሔም ፡ ወልዴ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Wolde)

የምትሰራውን ፡ ስለምትመዝን
በሚሆነው ፡ ነገር ፡ እኔ ፡ አላዝን
የማመልክህ ፡ አምላክ ፡ ለኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ
ለተገፉት ፡ ደራሽ ፡ በጸድቅ ፡ ትፈርዳለህ

አዝ:- በከፍታ ፡ በዝቅታ ፡ በሃዘንም ፡ በደስታ
አንተን ፡ አከብራለሁ ፡ ጌታን ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ
አንተን ፡ አከብራለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ

ለኔም ፡ ምታስበው ፡ በጐና ፡ መልካም ፡ ነው
ክፉ ፡ ሃሳብ ፡ አይደል ፡ የሰላም ፡ ሃሳብ ፡ ነው
ከኔ ፡ የበለጠ ፡ ለኔ ፡ ታስባለህ
ከእናት ፡ ከአባት ፡ ይልቅ ፡ ትጠነቀቃለህ

አዝ:- በከፍታ ፡ በዝቅታ ፡ በሃዘንም ፡ በደስታ
አንተን ፡ አከብራለሁ ፡ ጌታን ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ
አንተን ፡ አከብራለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ

በወይንም ፡ ሐረግ ፡ ውስጥ ፡ ፍሬ ፡ ባይገኝ
ትናንት ፡ የነበረኝ ፡ ዛሬ ፡ ባይኖረኝ
ማታ ፡ ባለቅስ ፡ እንኳን ፡ ጠዋት ፡ እስቃለህ
ስለዚህ ፡ ሁልጊዜ ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ

አዝ:- በከፍታ ፡ በዝቅታ ፡ በሃዘንም ፡ በደስታ
አንተን ፡ አከብራለሁ ፡ ጌታን ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ
አንተን ፡ አከብራለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ

ሰማዩ ፡ ቢጠራ ፡ ደመናም ፡ ባይኖርም
ምልክት ፡ ባይታይ ፡ ነፋስም ፡ ባይነፍስም
በገናዬን ፡ ይዤ ፡ እደረድራለሁ
ሸለቆ ፡ ሲሞላ ፡ በዓይኔ ፡ አየዋለሁ

አዝ:- በከፍታ ፡ በዝቅታ ፡ በሃዘንም ፡ በደስታ
አንተን ፡ አከብራለሁ ፡ ጌታን ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ
አንተን ፡ አከብራለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ