Bethlehem Wolde/Cher Neh/Balewuletayie
< Bethlehem Wolde | Cher Neh
ባለውለታዬ ጌታዬ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ መድህኔ ቅዱስ ስምህን እባርካለሁ ውለታህን አስታውሰዋለሁ (፪x)
ለኔ ነው መንከራተትህ መስቀል ተሸክመህ መውረድህ ለኔ የደም ላብ ያላበህ ፍቅር ነው እንዲህ ያስጨነቀህ ውለታህን አስታውሳለሁ ፈቅጄም አመልክሃለሁ ውለታህን አስታውሳለሁ ወድጄም አመልክሃለሁ
ባለውለታዬ ጌታዬ ...
ከአብ ዘንድ ለኔ የተሰጠ ትልቁ ስጦታዬ አንተ ነህ ይህ ሚስጥር ለኔ ተገልጾ መዳን ከአንተ ዘንድ ሆኖልኛል ውለታህን አስታውሳለሁ ፈቅጄም አመልክሃለሁ ውለታህን አስታውሳለሁ ወድጄም አመልክሃለሁ
ባለውለታዬ ጌታዬ ...
ልከፍለው አልችልም ውለታህን ያኔ ያረከውን በጐልጐታ ምስጋናን ሙገሳን ይዤ ላክብርህ ኢየሱስ ወዳጄ ውለታህን አስታውሳለሁ ፈቅጄም አመልክሃለሁ ውለታህን አስታውሳለሁ ወድጄም አመልክሃለሁ
ባለውለታዬ ጌታዬ ...