From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ሳልጠራጠር ፡ ሁሉን ፡ ቻይነቱን
አመልከዋለሁ ፡ እያየሁ ፡ ጉልበቱን/ሞገሱን
ሳልጠራጠር ፡ ሁሉን ፡ ቻይነቱን
አመልከዋለሁ ፡ እያየሁ ፡ ብርታቱን/ችሎቱን (፪x)
የእኔ/የእኛ ፡ ጌታ ፡ ሁሉንም ፡ ይችላል
እስኪ ፡ የቱ ፡ ምንስ ፡ አቅቶታል
የእኔ/የእኛ ፡ ጌታ ፡ ሁሉንም ፡ ይችላል
ኧረ ፡ የቱ ፡ ምንስ ፡ አቅቶታል (፪x)
ግዙፉን ፡ ተራራ ፡ ማደላደል ፡ ነው ፡ ዎይ
(እግዚአብሔር፡ ይህንን ፡ ይችላል)
ጥልቁን ፡ ሸለቆ ፡ ውሃ ፡ መሙላት ፡ ነው ፡ ዎይ
(እግዚአብሔር፡ ይህንን ፡ ይችላል)
የተዘጋውን ፡ ደጅ ፡ መከፋፈት ፡ ነው ፡ ዎይ
(እግዚአብሔር፡ ይህንን ፡ ይችላል)
ለጨለመው ፡ ሕይወት ፡ ብርሃን ፡ መስጠት ፡ ነው ፡ ዎይ
(እግዚአብሔር ፡ ይህንን ፡ ይችላል)
ይችላል ፡ ይችላል ፥ ይችላል ፡ እርሱ ፡ ይችላል
ይችላል ፡ ይችላል ፥ ይችላል ፡ ጌታ ፡ ይችላል
ይችላል ፡ ይችላል ፥ ይችላል ፡ በደንብ ፡ ይችላል
ይችላል ፡ ይችላል ፥ ይችላል ፡ ጌታ ፡ ይችላል
አንሱ ፡ ካለ ፡ ማንሳት ፡ እንጂ ፡ ድንጋዩን
መከራከር ፡ መሟገቱ ፡ ለምን
ሕያው ፡ ይሁን ፡ ይፈታ ፡ እንጂ ፡ አልዓዛር
ከሰው ፡ እኩል ፡ ይቁም ፡ ይብቃ ፡ ለክብር
ሁሉን ፡ ቻዩ ፡ ተናገረ ፡ ቃል ፡ አወጣ
እስከመቼ ፡ ያለማመን ፡ ብሎ ፡ ጣጣ
የማይሆነውን ፡ የሚያደርግ ፡ እንዲሆን
ያለረዳት ፡ ያለአጋዥ ፡ ብቻውን
ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ብቻ ፡ ለእግዚአብሔር (፫x)
ሳልጠራጠር ፡ ሁሉን ፡ ቻይነቱን
አመልከዋለሁ ፡ እያየሁ ፡ ጉልበቱን/ሞገሱን
ሳልጠራጠር ፡ ሁሉን ፡ ቻይነቱን
አመልከዋለሁ ፡ እያየሁ ፡ ብርታቱን/ችሎቱን (፪x)
የእኔ/የእኛ ፡ ጌታ ፡ ሁሉንም ፡ ይችላል
እስኪ ፡ የቱ ፡ ምንስ ፡ አቅቶታል
የእኔ/የእኛ ፡ ጌታ ፡ ሁሉንም ፡ ይችላል
ኧረ ፡ የቱ ፡ ምንስ ፡ አቅቶታል (፪x)
የሞተውን ፡ ተነስ ፡ ውጣ ፡ ማለት ፡ ነው ፡ ዎይ
(እግዚአብሔር፡ ይህንን ፡ ይችላል)
የታሰረውን ፡ ሰው ፡ ፈትቶ ፡ መልቀቅ ፡ ነው ፡ ዎይ
(እግዚአብሔር፡ ይህንን ፡ ይችላል)
እንቆቅልሽ ፡ ፍቺ ፡ መልስ ፡ መስጠት ፡ ነው ፡ ዎይ
(እግዚአብሔር፡ ይህንን ፡ ይችላል)
የጠላትን ፡ ሃሳብ ፡ ማፈራረስ ፡ ነው ፡ ዎይ
(እግዚአብሔር፡ ይህንን ፡ ይችላል)
ይችላል ፡ ይችላል ፥ ይችላል ፡ እርሱ ፡ ይችላል
ይችላል ፡ ይችላል ፥ ይችላል ፡ ጌታ ፡ ይችላል
ይችላል ፡ ይችላል ፥ ይችላል ፡ በደንብ ፡ ይችላል
ይችላል ፡ ይችላል ፥ ይችላል ፡ ጌታ ፡ ይችላል
|