Azeb Hailu/Single

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

|ዘማሪ=አዜብ ሐይሉ አዝማች ተራራው ግዙፍ ቢመስል ለእኔ እንጂ ለአንተ አይደለም በፊትህ ከባድ የሚሆን የማትችለው አንድ እንኳን የለም እግዚአብሔር አንተ ኃያል ነህ ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው ስታዝዘው የማይታዘዝህ ኤረ ከቶ የቱ ነው አምላኬ አንተ ኃያል ነህ ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው ስታዝዘው የማይታዘዝህ ኤረ ከቶ ምንድር ነው

፩) አንድ ነገር ሰማሁ እኔም አመንሁ እርሱን ኃይል የአንተ ብቻ የአንተ እንደሆነ ኃይል የአንተ ብቻ የአንተ እንደሆነ የሚጥል የሚያነሳ የሚገድል የሚያድን ኃይል የአንተ ብቻ የአንተ እንደሆነ ኃይል የአንተ ብቻ የአንተ እንደሆነ

አንተ ብርቱ ጌታ ከሆንህ የእኔ አባት ልረፍብህ እንጂ ልጠጋ በእምነት አንተ ብርቱ ጌታ ከሆንህ የእኔ አምላክ ሁሉን ለአንተ ትቼ ዝም ብዬ ላምልክህ

ተራራው ግዙፍ...

፪) የሰው ልጅ ያየለ ቢመስለው በዕውቀቱ ከፀሐይዋ በታች ነገር ሁሉ ከንቱ ከፀሐይዋ በታች ነገር ሁሉ ከንቱ አንተ ግን ጌታ ሆይ ለዘላለም ያው ነህ ሥራህ ሁሉ ግሩም ድንቅ የሆነልህ ሥራህ ሁሉ ግሩም ድንቅ የሆነልህ

አንተ ብርቱ ጌታ ...

ተራራው ገዝፎ ቢታይ ለእኔ እንጂ ለአንተ አይደለም በፊትህ ከባድ የሚሆን የማትችለው አንድ እንኳን የለም እግዚአብሔር አንተ ኃያል ነህ ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው ስታዝዘው የማይታዘዝህ ኤረ ከቶ የቱ ነው አምላኬ አንተ ኃያል ነህ ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው ስታዝዘው የማይታዘዝህ ኤረ ከቶ ምንድር ነው

ኤረ ለአምላኬ ይህቺ ምንድር ናት? በጣም ቀላል ናት በጣም ቀላል በጣም ቀላል ኤረ ለእግዚአብሔር ይህቺ ምንድር ናት? በጣም ቀላል ናት በጣም ቀላል በጣም ቀላል

ቀላል ነው (፲፪)

ስለዚህ ዝም ብዬ አመልክሃለሁ ስለዚህ አምላኬ አከብርሃለሁ ስለዚህ ጌታዬ አመልክሃለሁ ስለዚህ ዝም ብዬ አመልክሃለሁ

አመልክሃለሁ (፰)