From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Contact (at) Wikimezmur
የሰማያት ፡ ዳርቻ ፡ ሰሪ
የምድርም ፡ ሁሉ ፡ ፈጣሪ
አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ
እግዚአብሔር ፡ ኤልሻዳይ
ኧረ ፡ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ
እግዚአብሔር ፡ ሁሉን ፡ ቻይ
አላቋርጥ ፡ ማንኳኳቴን ፡ እስኪከፈትልኝ ፡ ደጁ
ፀሎቴንም ፡ እስኪሰማ ፡ እስኪዘረጋላኝ ፡ እጁ
ዘንበል ፡ እስኪል ፡ ከዙፋኑ ፡ እስኪበዛልኝ ፡ ምሕረቱ
ዝም ፡ አልልም ፡ አላቆምም ፡ መፈለጌን ፡ ማየት ፡ ፊቱን
እግዚአብሔር ፡ በዙፋኑ ፡ ያለው
ፀሎቴን ፡ ይሰማል ፡ አውቃልሁ
አምላኬ ፡ በማደሪያው ፡ ያለው
ይራራል ፡ ይምራል ፡ አምናለሁ (፪x)
እስኪለወጥ ፡ በምስጋና ፡ የለቅሶ ፡ የእንባ ፡ ጩኸቴ
ሙሉ ፡ ሆኖ ፡ እንኪመጣ ፡ እስኪለቀቅ ፡ በረከቴ
ከአንደበቱ ፡ እስኪወጣ ፡ የበረከት ፡ ንግግር
አልነሳም ፡ ዞር ፡ አልልም ፡ ከዙፋኑ ፡ ከእግሩ ፡ ስር
እግዚአብሔር ፡ በዙፋኑ ፡ ያለው
ፀሎቴን ፡ ይሰማል ፡ አውቃልሁ
አምላኬ ፡ በማደሪያው ፡ ያለው
ይራራል ፡ ይምራል ፡ አምናለሁ (፪x)
የተስፋውን ፡ ቃል ፡ አስቦ ፡ ሊፈጽመው ፡ እስኪነሣ
የምድሬኔም ፡ ኃጢአት ፡ በደል ፡ ይቅር ፡ ብሎ ፡ እስኪረሳ
ክብሩን ፡ ዳግም ፡ እስኪመልስ ፡ በቅዱሱ ፡ ማደሪያው
አላቆምም ፡ ክርክሬን ፡ እስኪነሣ ፡ ከስፍራው
የሚሰማ ፡ የሚመልስ ፡ የሚምር ፡ ነው ፡ የሚራራ (፪x)
በጎነቱ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ በሞገሱ ፡ የተፈራ (፪x)
ቸር ፡ እንደእርሱ ፡ ስለሌለ ፡ በምድር ፡ ቢሆን ፡ በሰማይ (፪x)
አንዲቷም ቀን አታልፍብኝ ፡ ያምላኬን ፡ ፊቱን፡ ሳላይ (፬x)
|