ላመሰግንህ ፡ እድል ፡ ስላገኘሁ (Lamesegeneh Edl Selagengehu) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(Volume)

ይችላል
(ይችላል)

ዓ.ም. (Year): 2005
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:22
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

ከኖርኩበት ከዚያ ከሞት ሰፈር
አስኮብልሎኝ ድንቁ ያንተ ፍቅር
እርግፍ አርጎ ሁሉን አስጣለና
አዲስ ህይወት ጎዳና
ኦ ድንቅ ነው መኖር ካንተ ጋራ
በሸለቆ ቢሆን በተራራ
ላመስግንህ እጆቼን አንስቼ
ከጠላቴ ወጥመድ ሁሉ አምልጬ

አዝ
(ላመሰግንህ እድል ስላገኘሁ
በዜማ ቃሌ አፌን እከፍታለሁ
ከፍ ላድርግህ መቅደስ ህ ልግባና
ባዲስ ዝማሬ ባዲሱ ምስጋና) x2
ተመስገን ፡ ዛሬም ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ ነገም ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ ሁሌም ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ ዘወትር ፡ ተመስገን

እሃሃሃ ፡ በእውነት ፡ እንደዳነ
አሃሃሃ ፡ በሕይወት ፡ እንዳለ ፡ ሰው
አሃሃሃ ፡ እስቲ ፡ በጐነትህን
አሃሃሃ ፡ እኔም ፡ ልዘምረው ፡ x2
አሃሃሃ ፡ ለሰው ፡ ሁሉ ፡ ልንገር
አሃሃሃ ፡ ማዳንህን ፡ ላውራ
አሃሃሃ ፡ ሁሌ ፡ በብርሃን
አሃሃሃ ፡ ቆሜ ፡ በተራራ x2

አዝ
(ላመሰግንህ እድል ስላገኘሁ
በዜማ ቃሌ አፌን እከፍታለሁ
ከፍ ላድርግህ መቅደስ ህ ልግባና
ባዲስ ዝማሬ ባዲሱ ምስጋና) x2
ተመስገን ፡ ዛሬም ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ ነገም ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ ሁሌም ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ ዘወትር ፡ ተመስገን

ድንቁ ፡ ፍቅርህ ፡ ካደናኝ ፡ በኋላ
በሕይወቴ ፡ ክቡር ፡ ጸጋን ፡ ሞላ
በመንግሥትህ ፡ እንድል ፡ ደፋ ፡ ቀና
ወግ ፡ ደረሰኝ ፡ እኔም ፡ ታሰብኩና
ቸርነትህ ፡ ኸረ ፡ እንደምን ፡ በዛ
ዝቅ ፡ ልበል ፡ ለክብርህ ፡ ልገዛ
በዝማሬ ፡ በብዙ ፡ ምሥጋና
ላሞጋግስህ ፡ ላድርግህ ፡ ገናና

አዝ
(ላመሰግንህ እድል ስላገኘሁ
በዜማ ቃሌ አፌን እከፍታለሁ
ከፍ ላድርግህ መቅደስ ህ ልግባና
ባዲስ ዝማሬ ባዲሱ ምስጋና) x2
ተመስገን ፡ ዛሬም ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ ነገም ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ ሁሌም ፡ ተመስገን
ተመስገን ፡ ዘወትር ፡ ተመስገን