ክቡር ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ (Kbur Egziabiher Hoy) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Azeb Hailu 3.jpg


(3)

አልበም
(Yechelal)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ ((2005))
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5፡15
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

ልዑል እግዚአብሔር ሆይ
ክቡር እግዚአብሔር ሆይ
ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ
የህይወቴ ዳኛ አንተ አይደለህም ወይ
የህመሜ ፈዋሽ አንተ አይደለህም ወይ
እግዚአብሔር ሆይ (2x)

በእግዚአብሔር የዳኔ አረ እንደኔ ማን ነው
ባህር ተከፍሎለት በደረቅ የሄደው
የረድኤት ጋሻ ሰይፍ ሆኖ ለቀንዴ
በአሳዳጆቼ ፊት ከፍ ያለ ነው ቀንዴ
ጌታዬ ውዴ

እሱ እግዚአብሔር ነው
ክቡር እግዚአብሔር ነው
ብርቱ እግዚአብሔር ነው
የህይወቴን ጨለማ ገለል ያደረገው
በብርሃን ተገልጦ ሰላም ይሁን ያለው
እግዚአብሔር ነው

የአባቶቼ አምላክ የፊት የጥንቶቹ
የነቢያት አምላክ የእምነት አርበኞቹ
የቅዱሳን አምላክ የነ ሐዋሪያቱ
ዛሬም የኔ ጌታ መች ዛለ ጉልበቱ
አቤት ብርታቱ

አሃሃሃ ዘምሪ ዘምሪ
አሃሃሃ ችተቀኚ ለክብሩ
አሃሃሃ ብዙ ድንቆች አሉ
አሃሃሃ ገና ያልተዘመሩ
አሃ አሃ ገና ያልተዘመሩ

አሃሃሃ ይለኛል በቀትር
አሃሃሃ ይለኛል በማታ
አሃሃሃ እየቀሰቀሰ
አሃሃሃ ምህረቱ የጌታ
አሃ አሃ ፍቅሩ የጌታ

እሱ እግዚአብሔር ነው
ክቡር እግዚአብሔር ነው
ብርቱ እግዚአብሔር ነው
የህይወቴን ጨለማ ገለል ያደረገው
በብርሃን ተገልጦ ሰላም ይሁን ያለው
እግዚአብሔር ነው

ዘምራለሁ እንጂ መች ዘመርኩኝ ገና
የጌታዬን ክብር የማዳኑን ዝና
ጽድቅ እንደ ፈረደ ለመበለቲቱ
ምስኪኑን ከትቢያ ከአመድ ላይ ማንሳቱ
በምህረቱ

አሃሃሃ ዘምሪ ዘምሪ
አሃሃሃ ችተቀኚ ለክብሩ
አሃሃሃ ብዙ ድንቆች አሉ
አሃሃሃ ገና ያልተዘመሩ
አሃ አሃ ገና ያልተዘመሩ

አሃሃሃ ይለኛል በቀትር
አሃሃሃ ይለኛል በማታ
አሃሃሃ እየቀሰቀሰ
አሃሃሃ ምህረቱ የጌታ
አሃ አሃ ፍቅሩ የጌታ

ልዑል እግዚአብሔር ሆይ
ክቡር እግዚአብሔር ሆይ
ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ
የህይወቴ ዳኛ አንተ አይደለህም ወይ
የህመሜ ፈዋሽ አንተ አይደለህም ወይ
እግዚአብሔር ሆይ