From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
አዜብ ፡ ኃይሉ (Azeb Hailu)
|
|
፮ (6)
|
6 (6)
|
ዓ.ም. (Year):
|
2024
|
ቁጥር (Track):
|
፯ (7)
|
ጸሐፊ (Writer):
|
kalkidan Girma (kalkidan GirmaProperty "Writer" has been marked for restricted use. )
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች (Albums by Azeb Hailu)
|
|
ተራራው ግዙፍ ቢመስል
ለእኔ እንጂ ለአንተ አይደለም
በፊትህ ከባድ የሚሆን
የማትችለው አንድ እንኳን የለም
እግዚአብሔር አንተ ኃያል ነህ
ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው
ስታዝዘው የማይታዘዝህ ኤረ ከቶ የቱ ነው
አምላኬ አንተ ኃያል ነህ
ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው
ስታዝዘው የማይታዘዝህ ኤረ ከቶ ምንድር ነው
፩) አንድ ነገር ሰማሁ እኔም አመንሁ እርሱን
ኃይል የአንተ ብቻ የአንተ እንደሆነ
ኃይል የአንተ ብቻ የአንተ እንደሆነ
የሚጥል የሚያነሳ የሚገድል የሚያድን
ኃይል የአንተ ብቻ የአንተ እንደሆነ
ኃይል የአንተ ብቻ የአንተ እንደሆነ
አንተ ብርቱ ጌታ ከሆንህ የእኔ አባት
ልረፍብህ እንጂ ልጠጋ በእምነት
አንተ ብርቱ ጌታ ከሆንህ የእኔ አምላክ
ሁሉን ለአንተ ትቼ ዝም ብዬ ላምልክህ
ተራራው ግዙፍ...
፪) የሰው ልጅ ያየለ ቢመስለው በዕውቀቱ
ከፀሐይዋ በታች ነገር ሁሉ ከንቱ
ከፀሐይዋ በታች ነገር ሁሉ ከንቱ
አንተ ግን ጌታ ሆይ ለዘላለም ያው ነህ
ሥራህ ሁሉ ግሩም ድንቅ የሆነልህ
ሥራህ ሁሉ ግሩም ድንቅ የሆነልህ
አንተ ብርቱ ጌታ ...
ተራራው ገዝፎ ቢታይ
ለእኔ እንጂ ለአንተ አይደለም
በፊትህ ከባድ የሚሆን
የማትችለው አንድ እንኳን የለም
እግዚአብሔር አንተ ኃያል ነህ
ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው
ስታዝዘው የማይታዘዝህ ኤረ ከቶ የቱ ነው
አምላኬ አንተ ኃያል ነህ
ሁሉ ለአንተ ቀላል ነው
ስታዝዘው የማይታዘዝህ ኤረ ከቶ ምንድር ነው
|