From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
በረጅምና ከፍ ባለው ዙፋን ላይ
ለተቀመጠው በሞገሱ በሰማይ
ስሙም እግዚአብሔር ያማልክቶች አምላክ
ይብዛለት ክብር ዘላለም ይባረክ
ወፎቹ ሲንጫጩ ጠዋት በማለዳ
ከጣራዬ በታች ካለሁበት ጓዳ
የቀኑ ጅማሬ የምስጋና እፍታ
ተነስቼ ልስጠው ለሚወደኝ ጌታ
በዙሪያዬ ያሉ ሁሉ ይቀስቀሱ
ጌታዬን ለማምለክ ድምፃቸውን ያንሱ
ስሙን የሚያከብር የማለዳ አምልኮ
ከማደሪያው ይግባ ቅዱስ ስሙን ባርኮ
አበዛለታለው አምልኮ አበዛለታለው ምስጋና
ለዚ ለገናና
አበዛለታለው ዝማሬ አበዛለታለው እልልታ
ለሚወደኝ ጌታ
በረጅምና ከፍ ባለው ዙፋን ላይ
ለተቀመጠው በሞገሱ በሰማይ
ስሙም እግዚአብሔር ያማልክቶች አምላክ
ይብዛለት ክብር ዘላለም ይባረክ
የዘላለም ንጉስ የዘላለም ጌታ
ማንም በማይቀርበው የክብር ከፍታ
በአእላፋት ቅኔ ዜማ ሃሌሉያ
እየተመለከ ሚኖር በማደሪያው
እኔም በዘመኔ ከትውልዴ ጋራ
የጌታን በጎነት ፅድቁን እንዳወራ
የከበረን እድል አግኝቻለሁና
ይገባዋል ልበል ለስሙ ምስጋና
እርሱ ጌታ ነው የጌቶች ጌታ የጌቶች ጌታ
ደግሞ ሚገባው ዝማሬ እልልታ ዝማሬ እልልታ
እርሱ አምላክ ነው ሃያል ገናና ሃያል ገናና
ደግሞ ሚገባው ክብር ምስጋና ክብር ምስጋና
የሚገባው ነው ክብር ምስጋና/4
አበዛለታለው አምልኮ አበዛለታለው ምስጋና
ለዚ ለገናና
አበዛለታለው ዝማሬ አበዛለታለው እልልታ
ለሚወደኝ ጌታ
እርሱ ጌታ ነው የጌቶች ጌታ የጌቶች ጌታ
ደግሞ ሚገባው ዝማሬ እልልታ ዝማሬ እልልታ
እርሱ አምላክ ነው ሃያል ገናና ሃያል ገናና
ደግሞ ሚገባው ክብር ምስጋና ክብር ምስጋና
የሚገባው ነው ክብር ምስጋና/4
|