From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
አዜብ ፡ ኃይሉ (Azeb Hailu)
|
|
፮ (6)
|
አልበም (6)
|
ዓ.ም. (Year):
|
2024
|
ቁጥር (Track):
|
፱ (9)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች (Albums by Azeb Hailu)
|
|
እግዚአብሔርን ፈልጉት ፈልጉት ትፀናላችሁ
እግዚአብሔርን ፈልጉት ፈልጉት ትፀናላችሁ (መገኘቱን)
የሚፈለግ የሚናፈቅ የሚወደድ ነው እርሱ
የሚፈለግ የሚናፈቅ የሚገኝም ነው እርሱ
የዚህ ዓለም ባለጠግነት (ምድር)
አይሞላውም የነፍሴን ክፍተት (የውስጤን) X2
ግን ከአንተ ጋራ ስሆን ኦ ጌታዬ (ስውል እየሱሴ)
በደስታ የተሞላ ነው ኑሮዬ (ሰላሜ ሞልቶ ይፈሳል በመንፈሴ) X2
እፈልጋለሁ ፍትህን ላየው
እፈልጋለሁ ድምፅን ልሰማው
እፈልጋለሁ ክብርህን ላየው
እፈልጋለሁ በእጄ ልነካው X2
በብዙ ሃብት በንብረት ተከቦ
ባርከኝ ይላል ዛሬም ፊትህ ቆሞ
ከቶ አልረካም አላረፈም ገና
ለባዶነቱ መልስ አንተ ነህና
ግን ከአንተ ጋራ ሲታገል ቆይቶ
ድኜ ቀረሁ አለ በጅህ ተነክቶ
እፈልጋለሁ...
ነፍሴ የፈለገችውን ከማግኘት በስተቀር
ምን ደስታ አላት በዚች ምድር
የነፍሴ ፍለጋ የነፍሴ መሻቷ
እየሱስ አንተ ነህ በጠዋት በማታ
ምትፈለግ ምትናፈቅ ምትወደድ ነህና
ምትፈለግ ምትናፈቅ ምትወደድ ነህና
|