እድንበታለሁ (Edinibetalehu) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Azeb Hailu 6.jpg


(6)

ሕያው አምላክ ነህ
(Hiyaw Amlak Neh)

ዓ.ም. (Year): 2024
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

ታላቅ የሆነውን
ስምህን እጠራለሁ
በሕይወቴ ዘመን እታመነዋለሁ

አመልጥበታለሁ እድንበታለሁ
ስምህን እጠራዋለሁ (x2)

እግዚአብሔር ስምህ እግዚአብሔር ነው
በዘመናት ሁሉ የተከበረ
ክኃይል እና ደግሞም ከብርታቱ
ያልተገታ ያልተከለከለ

ዛሬም ይሰራል ያድናል
ጨለማውን ብርሃን ያርደጋል/ተራራውን ሜዳ ያደርጋል
ስምህ በኃይል ይሰራል (x2)

ታላቅ...

አመልጥበታለሁ እድንበታለሁ
ስምህን እጠራዋለሁ
አመልጥብሃለሁ እድንብሃለሁ
ኢየሱስ እጠራሃለሁ

በላይ በታች ካለው ፍጥረት
ከሚመጣውም ዓለም
ከሚጠሩት ስሞች መሃከል
እንዳንተ ያለ የለም

ባህር አይታ የሸሸችህ
ተራሮችም የዘለሉት
አንተን አይተው እንደሆነ
መጽሐፍትም መሰከሩ

በሰማያት ላይ ታላቅ ነህ
በምድርም ላይ ታላቅ ነህ
በፍጥረት ሁሉ ታላቅ ነህ
ኢየሱስ/ጌታዬ አንተ ታላቅ ነህ (x2)

ኢየሱስ አንተ ታላቅ ነህ/ነው
(ጌታዬ ስምህ ታላቅ ነው)
አንተ እኮ እጅግ ታላቅ ነህ
(ኢየሱስ ስምህ ታላቅ ነው) (x2)

ኢየሱስ ስምህ ታላቅ ነው (x2)
ጌታዬ ስምህ ታላቅ ነው
ኢየሱስ ስምህ ታላቅ ነው

ወደአምላኬ ፊት የምቀርብበት
የምስጋና ድምጽ የማሰማበት
ሞገሴ ነው ስምህ ነው ድፍረቴ
መቀበያ ምላሽ የጸሎቴ

የሰማያትን ደጅ ይከፍታል
አባት ለልጁ መልስ ይሰጣል
ስምህ ኃይል አለው ይሰራል (x2)

ታላቅ...

አመልጥበታለሁ...
አመልጥብሃለሁ...

ኢየሱስ ስምህ ታላቅ ነው
(ጌታዬ ስምህ ታላቅ ነው)/(ኢየሱስ ስምህ ታላቅ ነው)
አንተ እኮ እጅግ ታላቅ ነህ
(ኢየሱስ ስምህ ታላቅ ነው) (x2)

ኢየሱስ ስምህ ታላቅ ነው
ጌታዬ ስምህ ታላቅ ነው
ኢየሱስ ስምህ ታላቅ ነው (x6)