From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
አዜብ ፡ ኃይሉ (Azeb Hailu)
|
|
፬ (4)
|
እንታረቅ (Enetareq)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፬ (2011)
|
ቁጥር (Track):
|
፰ (8)
|
ርዝመት (Len.):
|
5:26
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች (Albums by Azeb Hailu)
|
|
የታሰረችው ፡ ውርንጭላ ፡ ለኢየሱስ ፡ መቀመጫ
ታስፈልገዋለችና ፡ አምጧት ፡ በፍጥነት/በቶሎ ፡ ፍቱና (፪x)
ለምን ፡ ቢባል ፡ ሊከብርባት ፣ ለምን ፡ ቢባል ፡ ሊነግስባት
እራሱን ፡ በላዯ ፡ አድርጐ ፡ ኢየሩሳሌም ፡ ሊገባባት/ሊጓዝባት (፪x)
አዝ፦ የተፈታው ፡ እስራቴ ፡ የታወጀው ፡ አርነቴ
በቀራንዮ ፡ በጐልጐታ ፡ እራሱን ፡ ሲሰጥ ፡ ለእኔ ፡ ጌታ
ተፈጸመ ፡ ሲል ፡ ሲናገር ፡ የተጫነኝ ፡ ክፉ ፡ ቀንበር
ሲወድቅ ፡ አየሁ ፡ ሲሰባበር ፡ ይሁን ፡ ለእርሱ ፡ ብዙ ፡ ክብር
በድቅድቁ ፡ ጨለማ ፡ ተጥዬ ፡ ስደናበር
በጠበቀው ፡ ሰንሰለት ፡ ባማይፈታው ፡ እስር
እንድጠፋ ፡ ለሲዖል ፡ የታጨሁ ፡ በመሆኔ
በግፍ ፡ ነፍሴ ፡ ሊሰዋ ፡ ሊታረድ ፡ በጭካኔ
አዋጅ ፡ ወጣ ፡ ከሰማይ ፡ ከዙፋን ፡ ከመቅደሱ
ፍቷትና ፡ ትለቀቅ ፡ ተባለ ፡ ክብር ፡ ለእርሱ
አገኛታለሁ ፡ ብሎ ፡ የጐመጀው ፡ ጠላቴ
እፍረት ፡ ተከናነበ ፡ እኔም ፡ ጸና ፡ ጉልበቴ
አዝ፦ የተፈታው ፡ እስራቴ ፡ የታወጀው ፡ አርነቴ
በቀራንዮ ፡ በጐልጐታ ፡ እራሱን ፡ ሲሰጥ ፡ ለእኔ ፡ ጌታ
ተፈጸመ ፡ ሲል ፡ ሲናገር ፡ የተጫነኝ ፡ ክፉ ፡ ቀንበር
ሲወድቅ ፡ አየሁ ፡ ሲሰባበር ፡ ይሁን ፡ ለእርሱ ፡ ብዙ ፡ ክብር
አጥምዶብኝ ፡ ወጥመዱን ፡ እግሮቼ ፡ ስር ፡ ዘርግቶ
መረብ ፡ ውስጥ ፡ እንድገባ ፡ ፈልጐ ፡ እጅግ ፡ ጓጉቶ
መስሎት ፡ የተሳካለት ፡ የገባሁ ፡ በመዳፉ
ደስ ፡ ብሎት ፡ ጨፈረ ፡ ሊውጠኝ ፡ ይዞ ፡ በአፉ
የይሁዳው ፡ አንበሳ ፡ የቀራንዮ ፡ ጀግና
ጉልበተኛው ፡ ኢየሱስ ፡ ስመጥሩ ፡ ገናና
ፍፁም ፡ አይሆንም ፡ ብሎ ፡ ከሰማያት ፡ ወረደ
እራሱን ፡ ስለእኔ ፡ ሲሰጥ ፡ ጠላቴ ፡ ተዋረደ
አዝ፦ የተፈታው ፡ እስራቴ ፡ የታወጀው ፡ አርነቴ
በቀራንዮ ፡ በጐልጐታ ፡ እራሱን ፡ ሲሰጥ ፡ ለእኔ ፡ ጌታ
ተፈጸመ ፡ ሲል ፡ ሲናገር ፡ የተጫነኝ ፡ ክፉ ፡ ቀንበር
ሲወድቅ ፡ አየሁ ፡ ሲሰባበር ፡ ይሁን ፡ ለእርሱ ፡ ብዙ ፡ ክብር
ወገኖች ፡ የምስራች ፡ ተሸንፏል ፡ ዲያቢሎስ
የሞትን ፡ ጣር ፡ ባጠፋው ፡ በእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ በኢየሱስ
ከመስቀሉ ፡ ስር ፡ ያኔ ፡ አድቅቆታል ፡ ቀጥቅጦ
ለሚያምኑበት ፡ በሙሉ ፡ አስገዝቶታል ፡ ረግጦ
ወጥመዱ ፡ ተሰበረ ፡ ነፍሴ ፡ እንደወፍ ፡ በረረች
ሰይጣን ፡ ባዶ ፡ እጁን ፡ ቀረ ፡ ከግዞቱ ፡ አመለጠች
ሞትስ ፡ መውጊያው ፡ የታለ ፡ ጌታ ፡ ሞቶ ፡ ተነሳ
ከሲዖል ፡ ምርኮን ፡ ማርኮ ፡ በስልጣኑ ፡ ድል ፡ ነሳ
አዝ፦ የተፈታው ፡ እስራቴ ፡ የታወጀው ፡ አርነቴ
በቀራንዮ ፡ በጐልጐታ ፡ እራሱን ፡ ሲሰጥ ፡ ለእኔ ፡ ጌታ
ተፈጸመ ፡ ሲል ፡ ሲናገር ፡ የተጫነኝ ፡ ክፉ ፡ ቀንበር
ሲወድቅ ፡ አየሁ ፡ ሲሰባበር ፡ ይሁን ፡ ለእርሱ ፡ ብዙ ፡ ክብር (፪x)
|