From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
አዜብ ፡ ኃይሉ (Azeb Hailu)
|
|
፬ (4)
|
እንታረቅ (Enetareq)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፳ ፻ ፬ (2011)
|
ቁጥር (Track):
|
፫ (3)
|
ርዝመት (Len.):
|
5:16
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች (Albums by Azeb Hailu)
|
|
የማይደክም ፡ የማያረጅ ፡ ግሩም ፡ አምላክ ፡ ፍፁም ፡ ወዳጅ
ማይሸነፍ ፡ የማይረታ ፡ እርሱ ፡ ብቻውን ፡ ሁሌ ፡ ጌታ (፪x)
በሌሊቱ ፡ በአራተኛው ፡ ክፍል
በሌሊቱ ፡ እጅግ ፡ በከበደው
በሌሊቱ ፡ ታንኳዬም ፡ ሲጨነቅ
በሌሊቱ ፡ ማዕበሉ ፡ ሲገፋው
በሌሊቱ ፡ ድንገት ፡ ከተፍ ፡ አለ
በሌሊቱ ፡ ተገለጠ ፡ ጌታ
በሌሊቱ ፡ የሚያንገላታኝን
በሌሊቱ ፡ ሊገስጽ ፡ ሊመታ
የእኔ ፡ ጌታ ፡ አሃሃሃሃ ፡ የእኔ ፡ ተስፋ
የእኔ ፡ ክብር ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ (፪x)
አትፍሪ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ እያለ ፡ የሚያበረታኝን
እንደጌታዬ ፡ እንደኢየሱስ ፡ ከወዴት ፡ ላግኝ
በለመለመው ፡ መስክ ፡ ሚመራኝ ፡ በእረፍት ፡ ውኃ ዘንድ
አላገኝም ፡ በየትም ፡ ስፍራ ፡ እኔን ፡ የሚወድ
ይህ ፡ ነው ፡ አይባልም ፡ ብርታቱ
ሊያድን ፡ ፈጥኖ ፡ ደራሽነቱን
ጠበቃዬ ፡ ነው ፡ በጽድቅ ፡ ፍርዱ
እውነት ፡ ነው ፡ እርምጃው ፡ መንገዱ
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ ክንዱን ፡ ዘርግቶ
አቁሞኛል ፡ ከታች ፡ አንስቶ
የማዳኑን ፡ ብርታት ፡ ኃይሉን
ዘምራለሁ ፡ በሌት ፡ በቀን
የማይደክም ፡ የማያረጅ ፡ ግሩም ፡ አምላክ ፡ ፍፁም ፡ ወዳጅ
ማይሸነፍ ፡ የማይረታ ፡ እርሱ ፡ ብቻውን ፡ ሁሌ ፡ ጌታ (፪x)
ብሏልና ፡ እናንተ ፡ ደካሞች
ኑ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ከነ ፡ ሸክማችሁ
ስጡኝና ፡ የከበዳችሁን
እፎይ ፡ በሉ ፡ እስቲ ፡ ላሳርፋችሁ
እንደቃሉ ፡ የሚያስጨንቀኝን
ስተውለት ፡ ስሰጠው ፡ ነገሬን
የማላውቀው ፡ ሰላም ፡ ወረደብኝ
እፎይ ፡ አልኩኝ ፡ ረሳሁት ፡ ችግሬን
የእኔ ፡ ጌታ ፡ አሃሃሃሃ ፡ የእኔ ፡ ተስፋ
የእኔ ፡ ክብር ፡ ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ (፪x)
አትፍሪ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ እያለ ፡ የሚያበረታኝን
እንደጌታዬ ፡ እንደኢየሱስ ፡ ከወዴት ፡ ላግኝ
በለመለመው ፡ መስክ ፡ ሚመራኝ ፡ በእረፍት ፡ ውኃ ዘንድ
አላገኝም ፡ በየትም ፡ ስፍራ ፡ እኔን ፡ የሚወድ
|