ይገባሃል (Yegebahal) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(4)

እንታረቅ
(Enetareq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬(2011)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

 
ከሚያመልኩ ፡ ጋራ ፡ ከሚያነግሱህ ፡ ጋራ
እኔም ፡ ተስማምቼ ፡ ላንግስህ ፡ ማዳንህን ፡ ላውራ
ፊትህ ፡ ከሚሰግዱ ፡ በቅኔ ፡ ዝማሬ
ከእነርሱ ፡ ጋር ፡ አሜን ፡ ልበል
እኔም ፡ ተጨምሬ ፡ ላንግስህ ፡ እኔም ፡ ተጨምሬ
እኔም ፡ ተደምሬ ፡ ላምልክህ ፡ ኢኸው ፡ ለአንተ ፡ ክብሬ

ከመስዋዕት ፡ ይልቅ ፡ ምሥጋናን ፡ ወደሃል ፡ አህህ
በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ አምልኮ ፡ ከብረሃል
እንደዳዊት ፡ ጥሎ ፡ ማንነት ፡ ክብሩን ፡ አህህ
የሚዘልልህን ፡ ወደድከው ፡ ያንን ፡ አህህ

አዝይገባሃል (፫x) ፡ ከዚህ ፡ በላይ
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ አልተገኘምና ፡ አንተን ፡ መሳይ (፪x)

አምላክ ፡ በመቅደሱ ፡ ኪሩቤል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ አህህ
በረጅም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ ገኖ ፡ አህህ
ማደሪያውን ፡ ከበው ፡ ያሉት ፡ መላዕክት ፡ አህህ
አንዱም ፡ ለአንዱ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ሲሉት ፡ አህህ

አዝይገባሃል (፫x) ፡ ከዚህ ፡ በላይ
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ አልተገኘምና ፡ አንተን ፡ መሳይ (፪x)

ከሚያመልኩ ፡ ጋራ ፡ ከሚያነግሱህ ፡ ጋራ
እኔም ፡ ተስማምቼ ፡ ላንግስህ ፡ ማዳንህን ፡ ላውራ
ፊትህ ፡ ከሚሰግዱ ፡ በቅኔ ፡ ዝማሬ
ከእነርሱ ፡ ጋር ፡ አሜን ፡ ልበል
እኔም ፡ ተጨምሬ ፡ ላንግስህ ፡ እኔም ፡ ተጨምሬ
እኔም ፡ ተደምሬ ፡ ላምልክህ ፡ ኢኸው ፡ ለአንተ ፡ ክብሬ

ቀን ፡ ለቀን ፡ ሌሊትም ፡ ለሌሊት ፡ ሲያወጉ
በቋንቋቸው ፡ የእርሱን ፡ ክብር ፡ ሲተርኩ
ጨረቃና ፡ ፀሐይ ፡ እያብረቀረቁ
እግዚአብሔር ፡ ሰራን ፡ ሲሉ ፡ እያደነቁ

አዝይገባሃል (፫x) ፡ ከዚህ ፡ በላይ
በሰማይም ፡ በምድርም ፡ አልተገኘምና ፡ አንተን ፡ መሳይ (፪x)