ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (Qedus Neh Qedus) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(4)

እንታረቅ
(Enetareq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:55
ጸሐፊ (Writer): አዜብ ኃይሉ
(Azeb Hailu
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

አዝ፦ ቃላቶች ፡ ሁሉ ፡ አነሱብኝ ፡ ላመሰግንህ ፡ ፈልጌ
በማንስ ፡ ቋንቋ ፡ ላሞግስህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እንዴት ፡ አድርጌ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አምላክ ፡ ነህ
ንጉሤ ፡ ሆይ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ
ከዚህስ??? ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ለበልህ
ከዚህስ??? ፡ ሌላ ፡ ማን ፡ ልበልህ (፪x)

ኧረ ፡ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ እጅግ ፡ ገናና
ቃል ፡ የማይገልጸው ፡ ውበትህ ፡ ዝናህ
የምድር ፡ ቋንቋ ፡ የሰው ፡ ቃላት
ለእኔ ፡ አነሰብኝ ፡ ላዜምበት
በመላዕክቱ ፡ ቋንቋ ፡ ልሳን
ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ ፡ ለበልህ (፪x)

እስቲ ፡ ልጥራው ፡ ስምህን ፡ ፍፁም ፡ ቅዱስ ፡ የሆነውን
አንተ ፡ በራስህ ፡ ቅዱስ ፡ በማንነትህ ፡ ቅዱስ
በስራህ ፡ ሁሉ ፡ ቅዱስ ፡ በአደራረግህ ፡ ቅዱስ
አንተ ፡ ብቻህን ፡ ቅዱስ ፡ በማንነትህ ፡ ቅዱስ
በስራህ ፡ ሁሉ ፡ ቅዱስ ፡ በአደራረግህ ፡ ቅዱስ
ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ)
ቅዱስ ፡ ቅዱስ (ቅዱስ ፡ ኢየሱስ) (፪x)

አዝ፦ ቃላቶች ፡ ሁሉ ፡ አነሱብኝ ፡ ላመሰግንህ ፡ ፈልጌ
በማንስ ፡ ቋንቋ ፡ ላሞግስህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እንዴት ፡ አድርጌ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አምላክ ፡ ነህ
ንጉሤ ፡ ሆይ ፡ ንጉሥ ፡ ነህ
ከዚህስ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ለበልህ
ከዚህስ ፡ ሌላ ፡ ማን ፡ ልበልህ (፪x)

የዙፋንህን ፡ ክብር ፡ ድምቀት
የግዛትህን ፡ ወሰን ፡ ስፋት
የጌትነትህን ፡ ስልጣን ፡ ብቃት
የስምህን ፡ ዝና ፡ አለቅነት
በተመረጠው ፡ ቃልና ፡ ቅኔ
ብዘምር/ብቀኘው ፡ እንኳን ፡ አልረካም ፡ እኔ (፪x)

እስቲ ፡ ልጥራው ፡ ስምህን ፡ ፍፁም ፡ ቅዱስ ፡ የሆነውን
አንተ ፡ በራስህ ፡ ቅዱስ ፡ በማንነትህ ፡ ቅዱስ
በስራህ ፡ ሁሉ ፡ ቅዱስ ፡ በአደራረግህ ፡ ቅዱስ
አንተ ፡ ብቻህን ፡ ቅዱስ ፡ በማንነትህ ፡ ቅዱስ
በስራህ ፡ ሁሉ ፡ ቅዱስ ፡ በአደራረግህ ፡ ቅዱስ
ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ (ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ቅዱስ)
ቅዱስ ፡ ቅዱስ (ቅዱስ ፡ ኢየሱስ) (፬x)