ልዑል ፡ ማደሪያህ (Leul Maderiyah) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(4)

እንታረቅ
(Enetareq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬(2011)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

 
አዝ፦ ልዑል ፡ መጠጊያህ ፡ ሰፊ ፡ ነው
ልዑል ፡ መደሪያህ ፡ ምቹ ፡ ነው
ልዑል ፡ ማረፊያህ ፡ ሰላም ፡ ነው
ያለሥጋት ፡ እኖራለሁ (፪x)

ሊያስፈራሩኝ ፡ የሞከሩ ፡ ሊያጐሳቁሉኝ ፡ የጣሩ
አሏዋለላቸውም ፡ በቃ ፡ ልዑል ፡ አምላክ ፡ አለኝ ፡ ለካ
ስለገባሁ ፡ በመዳፉ ፡ ጠላቶቼ ፡ እንዲያው ፡ ለፉ
በእኔና ፡ በእነርሱ ፡ መኻል ፡ ብርቱ ፡ ቅጥር ፡ ጌታ ፡ ሰርቷል
(፪x)

ሃ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ
ሃ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ

በ???? ፡ ባዮች ፡ ተሸፍኜ ፡ በክንፎችህም ፡ ተማምኜ
እውነት ፡ እንደ ፡ ጋሻ ፡ ከቦኝ ፡ ከአደጋ ፡ ሁሉ ፡ አስጥሎኝ
ሳልደነግጥም ፡ ሳልፈራ ፡ ኢኸው ፡ ስኖር ፡ ከአንተ ፡ ጋራ
መኖሪያህ ፡ ተመችቶኛል ፡ ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ያሻኛል
(፪x)

አዝ፦ ልዑል ፡ መጠጊያህ ፡ ሰፊ ፡ ነው
ልዑል ፡ መደሪያህ ፡ ምቹ ፡ ነው
ልዑል ፡ ማረፊያህ ፡ ሰላም ፡ ነው
ያለሥጋት ፡ እኖራለሁ (፪x)

አንተ ፡ መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ መሸህሰጊያዬ ፡ ነው ፡ ስምህ
ክፉ ፡ ነገር ፡ አይቀርበኝም ፡ መቅሰፍትም ፡ አያገኘኝም
በመንገዴ ፡ እንዲጠብቁኝ ፡ መላእክትህን ፡ ታዛለህ
እግሬም ፡ እንዳይሰናከል ፡ በእጆችህ ፡ ታነሳኛለህ
(፪x)

ሃ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ
ሃ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ
ሃ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ
ሃ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ