From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ላሞግሰው ፡ ዙፋንህን ፡ ላደናንቅ
ከእግሮችህ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ ቅኔን ፡ ላፈልቅ
አንደበቴን ፡ ቀድሼ ፡ ዜማ ፡ ላፈስ
ጌታ ፡ ልልህ ፡ መጣሁ ፡ ክበር ፡ ንገሥ
እንዲህ ፡ ከሚሉ ፡ ጋራ ፡ ልተባበር
እኔም ፡ የእራሴን ፡ ፈንታ ፡ ልጨምርልህ
ይሄም ፡ ትንሽ ፡ ነው ፡ ለአንተ ፡ አይበዛምና
ከናፍርቶቼ ፡ ይጥሩህ ፡ ብለው ፡ ገናና ፡ አንተ ፡ ገናና
አንተ ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ገናና (፪x)
በላይ ፡ ነህ ፡ ከዚህም ፡ በላይ ፡ ነህ
በላይ ፡ ነህ ፡ ከዚያም ፡ በላይ ፡ ነህ (፪x)
ከሰማነው ፡ እና ፡ ካየነው
በላይ ፡ ነህ ፡ ከዚህም ፡ በላይ ፡ ነህ
ከዘመርነው ፡ ከሰበክነው
በላይ ፡ ነህ ፡ ከዚያም ፡ በላይ ፡ ነህ (፪x)
የለም (፫x) ፡ ሌላ ፡ ጌታ ፡ የለም
የለም(፫x) ፡ ሌላ ፡ ንጉሥ ፡ የለም
የለም (፫x) ፡ ሌላ ፡ አዳኝ ፡ የለም
የለም (፫x) ፡ ሌላ ፡ ገዢ ፡ የለም
ሌላ ፡ ጌታ ፡ የለም ፣ ሌላ ፡ ንጉሥ ፡ የለም
ሌላ ፡ አዳኝ ፡ የለም ፣ ሌላ ፡ ገዢ ፡ የለም (፪x)
በእውነትና ፡ በመንፍስ ፡ ስትመለክ
ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ በፊትህ ፡ ሲል ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ
ቋንቋው ፡ ሁሉ ፡ ስለአንተ ፡ ዝና ፡ ሲያወራ
ሲባል ፡ ከአማልክት ፡ ሁሉ ፡ ነህ ፡ የተፈራህ
እንዲህ ፡ ከሚሉ ፡ ጋራ ፡ ልተባበር
እኔም ፡ የእራሴን ፡ ፈንታ ፡ ልጨምርልህ
ይሄም ፡ ትንሽ ፡ ነው ፡ ለአንተ ፡ አይበዛምና
ገና ፡ ፍጥሮችህ ፡ ይጥሩህ ፡ ብለው ፡ ገናና ፡ አንተ ፡ ገናና
አንተ ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ገናና (፪x)
በላይ ፡ በሰማይ ፡ ላለው ፡ በዙፋኑ
ለሚገዙለት ፡ እልፍ ፡ ቅዱሳኑ
ለሚባርኩ ፡ ስሙን ፡ በዝማሬ
አምላክ ፡ ለሆነው ፡ ጥንትም ፡ ቢሆን ፡ ዛሬ (፪x)
እኔም ፡ አለኝ ፡ አምልኮ
እኔም ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና
እኔም ፡ አለኝ ፡ ዕልልታ
በአመታት ፡ መካከል
ጸንቶ ፡ ለሚኖረው
ለጌቶቹ ፡ ጌታ (፪x)
ለጌቶቹ ፡ ጌታ
ለነገሥታት ፡ ንጉሥ
ለጌቶቹ ፡ ጌታ (፪x)
|