From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ከቶ ፡ አልደከመም ፡ ጉልበቱ
ከቶም ፡ አልደነዘም ፡ ስለቱ
ዛሬም ፡ አልፈዘዘም ፡ ውበቱ
ይገርማል ፡ የቃልህ ፡ ጽናቱ
አሁንም ፡ ይሰራል ፡ ያው ፡ ነው
በፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ገዢ ፡ ነው
ሰማያት ፡ ቢያልፉም ፡ ምድር
ቃልህ ፡ ለዘለዓለም ፡ ክቡር
አዝ፦ ክቡር (፫x) ፡ ቃሉ ፡ የእግዚአብሔር
ክቡር (፫x) ፡ ድምጹ ፡ የእግዚአብሔር
ክቡር (፫x) ፡ የእርሱ ፡ ንግግር
ድምጹ ፡ ተራራውን ፡ ያቀልጣል
ጠንካራውን ፡ ዝግባ ፡ ይቆርጣል
ጥቅጥቅ ፡ ያለውን ፡ ጫካ ፡ ይገልጣል
ጌታዬ ሆይ ድምጽህ ያስፈራል
ቃልህ ፡ ሰማያትን ፡ አጽንቷል
ምድርን ፡ ደግሞ ፡ መስርቷል
ሕያውን ፡ ግዑዙንም ፡ ሰርቷል
በዘለዓለም ፡ ክብሩ ፡ ይኖራል
አዝ፦ ክቡር (፫x) ፡ ቃሉ ፡ የእግዚአብሔር
ክቡር (፫x) ፡ ድምጹ ፡ የእግዚአብሔር
ክቡር (፫x) ፡ የእርሱ ፡ ንግግር
ወጀብ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ አውሎ ፡ ንፋሱ
ሰምቶ ፡ መልስ ፡ ያልሰጠው ፡ ለድምጹ
ግዑዝ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ ሕያው ፡ ፍጥረት
ሰምተው ፡ ማይታዘዙት
በሰማያት ፡ ያሉ ፡ በምድር
ይገዛሉ ፡ ለእግዚአብሔር
በሁሉ ፡ ላይ ፡ ብርቱ ፡ ገናና
የእኔ ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነውና
ከቶ ፡ አልደከመም ፡ ጉልበቱ
ከቶም ፡ አልደነዘም ፡ ስለቱ
ዛሬም ፡ አልፈዘዘም ፡ ውበቱ
ይገርማል ፡ የቃልህ ፡ ጽናቱ
አሁንም ፡ ይሰራል ፡ ያው ፡ ነው
በፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ገዢ ፡ ነው
ሰማያት ፡ ቢያልፉም ፡ ምድርም
ቃልህ ፡ ለዘለዓለም ፡ ክቡር
አዝ፦ ክቡር (፫x) ፡ ቃሉ ፡ የእግዚአብሔር
ክቡር (፫x) ፡ ድምጹ ፡ የእግዚአብሔር
ክቡር (፫x) ፡ የእርሱ ፡ ንግግር
|