ፈራለሁ (Feralehu) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(4)

እንታረቅ
(Enetareq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2011)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 6:07
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

ህልውናህን ፡ ሳጣው ፡ ከጐኔ
ክብርህን ፡ ማየቱ ፡ ሲሳነው ፡ ዓይኔ
ድምፅህ ፡ ሲጠፋ ፡ ሲርቀኝ ፡ ከእኔ
ያኔ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ መሪር ፡ ሀዘኔ
ያኔ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ መሪር ፡ ሀዘኔ
ያኔ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ መሪር ፡ ሀዘኔ

ፈራለሁ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ፈራለሁ
ሰጋለሁ ፡ ድምፅህ ፡ ሲጠፋ ፡ ሰጋለሁ
ወደ ፡ ጉድጓድ ፡ የሚወርዱትን ፡ መስላለሁ
ሆሆ ፡ ፈራለሁ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ፈራለሁ

ስትደበቀኝ ፡ ሲሰወር ፡ ፊትህ
ዝግ ፡ ሲሆንብኝ ፡ ደጅ ፡ በብረት
ማን ፡ አለኝ ፡ ብዬ ፡ በማን ፡ ልመካ
ኃይሌም ፡ ጉልበቴ ፡ ፊትህ ፡ ነው ፡ ለካ (፪x)

አትሰወርብኝ ፡ አትደበቀኝ
ሰምተህ ፡ እንዳልሰማ ፡ አትሁንብኝ
አትሰወርብኝ ፡ አትደበቀኝ
አይተህ ፡ እንዳላየ ፡ አትሁንብኝ (፪x)

ህልውናህን ፡ ሳጣው ፡ ከጐኔ
ክብርህን ፡ ማየቱ ፡ ሲሳነው ፡ ዓይኔ
ድምፅህ ፡ ሲጠፋ ፡ ሲርቀኝ ፡ ከእኔ
ያኔ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ መሪር ፡ ሀዘኔ
ያኔ ፡ ነው ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ መሪር ፡ ሀዘኔ
ያኔ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ መሪር ፡ ሀዘኔ

ፈራለሁ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ፈራለሁ
ሰጋለሁ ፡ ድምፅህ ፡ ሲጠፋ ፡ ሰጋለሁ
ወደ ፡ ጉድጓድ ፡ የሚወርዱትን ፡ መስላለሁ
ሆሆ ፡ ፈራለሁ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ፈራለሁ