እንታረቅ (Enetareq) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(4)

እንታረቅ
(Enetareq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬(2011)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

አፍቅሮኝ ፡ ፍቅርን ፡ አስተማረኝ
የማረኝ ፡ ምህረት ፡ አድርጊ ፡ ያለኝ
በጌታ ፡ ለካ ፡ ይህም ፡ ይቻላል
ለአሳዳጅ ፡ ምህረት ፡ ይደረጋል

ገዳዬን ፡ በእጅህ ፡ ላይ ፡ አግኝቶ
መመለስ ፡ መንገድ ፡ አሳይቶ
እንዲህ ፡ ነው ፡ ለካ ፡ ፍቅር ፡ ማለት
ሁሉንም ፡ መቀበል ፡ በምህረት
(፪x)

ምህረት ፡ አግኝቼ ፡ ምህረት ፡ አሰጣለሁ
ይቅር ፡ ተብዪ ፡ ይቅር ፡ እላለሁ (፪x)

ህግ??? ፡ ሳናደርግ ፡ በመሃከላችን
መስዋዕት ፡ ለማቅረብ ፡ ምነው ፡ ችኮላችን
ይቅር ፡ መባባሉ ፡ ማንንስ ፡ ገደለ
ተቆጥተን ፡ መሸ ፡ ዋል ፡ አደርም ፡ አለ

እንታረቅ ፡ አሃሃሃ ፡ እንታረቅ
እንታረቅ ፡ አሆሆሆ ፡ እንታረቅ (፪x)

አሁን ፡ እንታረቅ ፡ እርስ ፡ በእርሳችን
ሳንሰዋ ፡ በፊት ፡ መስ ፡ ዋዕታችንን
በአምላካችን ፡ ፊት ፡ እስቲ ፡ እንተቃቀፍ
የሰጠውንም ፡ ቃል ፡ ከቶ ፡ አንተላለፍ

እንታረቅ ፡ አሃሃሃ ፡ እንታረቅ
እንታረቅ ፡ አሆሆሆ ፡ እንታረቅ (፪x)
ምህረት ፡ አግኝቼ ፡ ምህረት ፡ አሰጣለሁ
ይቅር ፡ ተብዪ ፡ ይቅር ፡ እላለሁ (፪x)

ታናሹን ፡ ከታላቁ ፡ እኩል
በአንድነት ፡ ማቀፍ ፡ መጠየቅ
በዳዩን ፡ መጠየቅ ፡ ይቅርታ
ይሄ ፡ ነው ፡ ወንጌሉ ፡ የጌታ
ለአፍቃሪ ፡ ፍቅር ፡ መስጠትማ
ያለ ፡ ነው ፡ በዓለም ፡ ከተማ
ጨካኝ ፡ ነው ፡ የሚሉትን ፡ ክፉ
ይቻላል ፡ በወንጌል/በጌታ ፡ ማቀፉ
(፪x)

ምህረት ፡ አግኝቼ ፡ ምህረት ፡ አሰጣለሁ
ይቅር ፡ ተብዪ ፡ ይቅር ፡ እላለሁ (፪x)
እንታረቅ ፡ አሃሃሃ ፡ እንታረቅ
እንታረቅ ፡ አሆሆሆ ፡ እንታረቅ (፪x)