እንሂድ ፡ ሲሉኝ (Enehid Silugn) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(4)

እንታረቅ
(Enetareq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬(2011)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

 
እንሂድ ፡ ሲሉኝ ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ቤት
ደስ ፡ ካለኝ ፡ ሓሴት ፡ ካደረኩት
ስሄድማ ፡ ስገባ ፡ በፊቱ ፡ ሲቀበለኝ ፡ በብዙ ፡ ምህረቱ
ይጨምራል ፡ ይበዛል ፡ ደስታዬ ፡ በመንፈሱ ፡ ሲነካኝ ፡ ጌታዬ
በረከቱን ፡ ባዘዘበት ፡ ስፍራ ፡ ከዚያ ፡ ልሆን ፡ ከቅዱሳን ፡ ጋራ
ደግነቱን ፡ ባዘዘበት ፡ ስፍራ ፡ ከዚያ ፡ ልሆን ፡ ከወገኖች ፡ ጋራ

አምላኬ ፡ ሆይ ፡ በቤትህ ፡ ሰላም ፡ አለ
ያዘነውን ፡ የሚያጽናና ፡ እያባበለ (፪x)
በዓለም ፡ ካለው ፡ የተለየ ፡ ሰላም ፡ ደስታ
አግኝቻለሁ ፡ ወደ ፡ ቤትህ ፡ እኔ ፡ ስመጣ (፪x)

ወደ ፡ ቤትህ ፡ ልገስግስ ፡ በመንፈስህ ፡ እንድዳሰስ
ወደ ፡ ፊትህ ፡ ልገስግስ ፡ በእጆችህ ፡ እንድዳሰስ
ወደ ፡ ክብርህ ፡ ልገስግስ ፡ በውበትህ ፡ እንዲለኝ ፡ ደስ
ወደ ፡ ፀጋህ ፡ ልገግስ ፡ በመንፈስ ፡ እንዲለኝ ፡ ደስ

ሁል ፡ ጊዜ ፡ በፊትህ ፡ የሚቆሙ
ጥበብህን ፡ ከአንደበትህ ፡ የሚሰሙ (፪x)
ባሪያዎችህ ፡ ኧረ ፡ እንደምን ፡ የታደሉ
በማደሪያህ ፡ ደፋ ፡ ቀና ፡ ሁሌ ፡ የሚሉ
በቤትህ ፡ ደፋ ፡ ቀና ፡ ሁሉ ፡ ሚሉ

ወደ ፡ ቤትህ ፡ ልገስግስ ፡ በመንፈስህ ፡ እንድዳሰስ
ወደ ፡ ፊትህ ፡ ልገስግስ ፡ በእጆችህ ፡ እንድዳሰስ
ወደ ፡ ክብርህ ፡ ልገስግስ ፡ በውበትህ ፡ እንዲለኝ ፡ ደስ
ወደ ፡ ፀጋህ ፡ ልገግስ ፡ በመንፈስ ፡ እንዲለኝ ፡ ደስ

ልዑል ፡ መጠጊያ ፡ ጥላ
ለዚህ ፡ ዓለም ፡ ሐሩር ፡ ከለላ
መኖሪያ ፡ ነህ ፡ በኧረፍት
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ የአንተ ፡ ቢት
ሰው ፡ ሁሉ ፡ ይኖራል ፡ ታምኖ
ሳይሰጋ ፡ ምን ፡ ይሆናል ፡ ብሎ
በቤትህ ፡ በመቅደስህ ፡ ምትሸከም ፡ አንተ ፡ ነህ

እንሂድ ፡ ሲሉኝ ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ቤት
ደስ ፡ ካለኝ ፡ ሓሴት ፡ ካደረኩት
ስሄድማ ፡ ስገባ ፡ በፊቱ ፡ ሲቀበለኝ ፡ በብዙ ፡ ምህረቱ
ይጨምራል ፡ ይበዛል ፡ ደስታዬ ፡ በመንፈሱ ፡ ሲነካኝ ፡ ጌታዬ
በረከቱን ፡ ባዘዘበት ፡ ስፍራ ፡ ከዚያ ፡ ልሆን ፡ ከቅዱሳን ፡ ጋራ
ደግነቱን ፡ ባዘዘበት ፡ ስፍራ ፡ ከዚያ ፡ ልሆን ፡ ከወገኖች ፡ ጋራ