በየቀኑ ፡ በየዕለቱ (Beyeqenu Beyeletu) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(4)

እንታረቅ
(Enetareq)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬(2011)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

 
አዝ፦ በየቀኑ ፡ በየእለቱ ፡ በየማለዳው ፡ የማየው
የጌታዬን ፡ ብዙ ፡ ምህረት ፡ ብዙ ፡ ፍቅሩን ፡ ብቻ ፡ ነው
በየእለቱ ፡ በየቀኑ ፡ በየማለዳው ፡ የማየዉ
የኢየሱሴን ፡ ብዙ ፡ ምህረት ፡ ብዙ ፡ ፍቅሩን ፡ ብቻ ፡ ነው

የወደዳቸውን ፡ ፈጽሞ ፡ እስከመጨረሻው ፡ ወደደ
ልጆቹን ፡ ከበደል ፡ ሊያነፃ ፡ በእራሱ ፡ ላይ ፡ ሞትን ፡ ፈረደ
ከሞት ፡ ይልቅ ፡ እጅግ ፡ ያየለ ፡ የበረታ ፡ ፍቅር ፡ ይዞት
ኢየሱስ ፡ እራሱን ፡ ከፈለ ፡ የእኔ ፡ መጥፋት ፡ አሳዝኖት
እነሆ ፡ ሲነጋና ፡ ሲመሽ ፡ ይህን/የእርሱን ፡ ፍቅር ፡ አስታውሰዋለሁ
ሌለ ፡ ምሰጠው ፡ የለምና ፡ ተመስገን ፡ ከፍ ፡ በል ፡ እለዋለሁ
(፪x)

አዝ፦ በየቀኑ ፡ በየእለቱ ፡ በየማለዳው ፡ የማየው
የጌታዬን ፡ ብዙ ፡ ምህረት ፡ ብዙ ፡ ፍቅሩን ፡ ብቻ ፡ ነው
በየእለቱ ፡ በየቀኑ ፡ በየማለዳው ፡ የማየዉ
የኢየሱሴን ፡ ብዙ ፡ ምህረት ፡ ብዙ ፡ ፍቅሩን ፡ ብቻ ፡ ነው

ፍቅር ፡ ምን ፡ እንደሆነ ፡ ታወቀ ፡ በስራው ፡ በኃይሉ ፡ በርትቶ
ሰማይን ፡ ከምድር ፡ አስታረቀ ፡ በምህረቱ ፡ ጉልበት ፡ ጐትቶ
የጥሉ ፡ ግድግዳ ፡ ፈረሰ ፡ ሆነ ፡ እርቅ ፡ ሰላም ፡ ደስታ
የራቀው ፡ በሙሉ ፡ ቀረበ ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዙፋን ፡ በጌታ
አቤት ፡ ይሄ ፡ ጌታ ፡ ቸርነቱ ፡ አደራረጉ ፡ አስገርሞኛል
በእውቀት ፡ በችሎታና ፡ ጥበቡ ፡ ወደ ፡ ፍቅሩ ፡ ግዛት ፡ አድርሶኛል
(፪x)

እንዴት ፡ እንደሆነ ፡ ባላውቅም ፡ ኧረ ፡ ለምን ፡ ለምን
ግን ፡ ይህንን ፡ ብቻ ፡ አውቃለሁ ፡ እኔ ፡ መወደዴን
ይህንን ፡ ብቻ ፡ አውቃለሁ ፡ የወደደኝን
በጉያው ፡ በእቅፉ ፡ አስገብቶ ፡ እንደሰወረኝ
አውቃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ሁልጊዜ ፡ እንደሚያስብልኝ (፪x)

አዝ፦ በየቀኑ ፡ በየእለቱ ፡ በየማለዳው ፡ የማየው
የጌታዬን ፡ ብዙ ፡ ምህረት ፡ ብዙ ፡ ፍቅሩን ፡ ብቻ ፡ ነው
በየእለቱ ፡ በየቀኑ ፡ በየማለዳው ፡ የማየዉ
የኢየሱሴን ፡ ብዙ ፡ ምህረት ፡ ብዙ ፡ ፍቅሩን ፡ ብቻ ፡ ነው