ይሄ ፡ ነው (Yehie New) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Azeb Hailu 1.png


(1)

እምቢ
(Embi)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

እጅጉን ፡ ሲራራ ፡ በብዙ ፡ ሲምር
ከቶ ፡ ያበቃለትን ፡ የሞት ፡ ፍርድ ፡ ሲሽር
ሲስብ ፡ ወደራሱ ፡ ለክብር ፡ መንግስቱ
እኔ ፡ እርሱን ፡ የማውቀው ፡ በሰፊ ፡ ትዕግስቱ

መክሮ ፡ ሲመልስ ፡ ለክብር ፡ ሲያበቃ
ውጦ ፡ ከሚያስቀር ፡ ከረግረጉ ፡ ጭቃ
ታሪክ ፡ ቀይሮ ፡ ሥምንም ፡ ሲለውጥ
ነጥቆም ፡ ሲታደግ ፡ ካንሸራታቹ ፡ ድጥ (፪x)

አዝ፦ይሄ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ
ይሄ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ የምለው
ይሄ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ቸር ፡ ያልኩት
እግዚአብሔር : እኔ ፡ የወደድኩት (፪x)

የተራበው ፡ ሲጠግብ ፡ ሲረካ ፡ ጠጥቶ
ሲድን ፡ ከጠላቱ ፡ ወደ ፡ አምላኬ ፡ ሸሽቶ
በኖርኩበት ፡ ዘመን ፡ ይሄንን ፡ አውቃለሁ
መልካም ፡ ቸር ፡ እረኛ ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ማነው

ከጥላው ፡ በታች ፡ ማረፍ ፡ የወደደ
በዓለም ፡ በረሃ ፡ ከስሎ ፡ የነደደ
ሸክሙ ፡ ሲራገፍ ፡ እፎይ ፡ ሲል ፡ ሲቀለው
በርሱም ፡ ሲታሰብ ፡ ባይኔ ፡ አይቻለሁ (፪x)

አዝ፦ይሄ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ
ይሄ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ የምለው
ይሄ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ቸር ፡ ያልኩት
እግዚአብሔር : እኔ ፡ የወደድኩት (፪x)

ክፉኛ ፡ ተወግቶ ፡ ልቡ ፡ ለቆሰለ
በኃዘን ፡ ተከቦ ፡ አበቃልኝ ፡ ላለ
ወዳጅ ፡ ይሆነዋል ፡ ጌታ ፡ ተጠግቶ
ቁስሉን ፡ ያክመዋል ፡ በዘይት ፡ ቀብቶ

ቀና ፡ ሲያደርገው ፡ አንገቱን ፡ ላይደፋ
የሚጤሰውን ፡ ጧፉን ፡ ሳያጠፋ
አትሞትም ፡ በሕይወት ፡ ትኖራለህ ፡ ሲለው
የአምላኬን ፡ ፍቅር ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ (፪x)

አዝ፦ይሄ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ
ይሄ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ የምለው
ይሄ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ቸር ፡ ያልኩት
እግዚአብሔር : እኔ ፡ የወደድኩት (፪x)

አለኝ ፡ ሊቀ-ካህን ፡ በላይ ፡ በሰማይ
አዝኖ ፡ የሚራራ ፡ ድካሜን ፡ የሚያይ
ለበደሌ ፡ ስርየት ፡ ለሐጥያቴ ፡ ይቅርታ
ሰጠኝ ፡ በምህረቱ ፡ ይሄ ፡ መልካም ፡ ጌታ

አባባ ፡ የሚል ፡ የልጅነት ፡ መንፈስ
ውስጤ ፡ አፈሰሰ ፡ ቸሩ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ
መንፈሱን ፡ ታጥቅኩኝ ፡ ድኛለሁኝ ፡ በቃ
ሞትና ፡ እርግማን ፡ ከእንግዲህ ፡ አበቃ

አዝ፦ይሄ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ
ይሄ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ የምለው
ይሄ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ቸር ፡ ያልኩት
እግዚአብሔር፡ : እኔ ፡ የወደድኩት (፬x)