የዳዊት (Yedawit) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Azeb Hailu 1.png


(1)

እምቢ
(Embi)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

የዳዊት ፡ የአብርሃም ፡ ልጅ ፡ ያሉት
ነብያት ፡ ቀድመው ፡ የተረኩት
በድንግል ፡ በማርያም ፡ ያደረ
የትውልድ ፡ ሐረግ ፡ ያስቆጠረ

ልደቱ ፡ በቤተልሔም
በንጉሥ ፡ በሄሮድስ ፡ ዘመን
እረኞች ፡ በግርግም ፡ ያዩት
ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ መድኃኒት

የይሁዳ ፡ ምድር ፡ አንቺ ፡ ቤተልሔም
ከይሁዳ ፡ ግዛቶች ፡ ከቶ ፡ አታንሺም
እስራኤልን ፡ የሚጠብቅ ፡ መስፍን ፡ ካንቺ ፡ ይወጣል
ተብሎ ፡ እንደተነገረ ፡ ኢየሱስ ፡ ተወልዷል

መልአኩ ፡ ወደ ፡ ማርያም ፡ ገብቶ
የሰላም ፡ ድምጹን ፡ አሰምቶ
አምላኬ ፡ ፀጋ ፡ የሞላብሽ
ማርያም ፡ ሆይ ፡ በይ ፡ ደስ ፡ ይበልሽ

እነሆ ፡ ልጅን ፡ ትወልጃለሽ
ሥሙንም ፡ ኢየሱስ ፡ ትይዋለሽ
በያዕቆብ ፡ ቤት ፡ ሁሉ ፡ ይነግሳል
የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ እርሱም ፡ ይባላል

ነፍሴ ፡ ጌታን ፡ ትባርከው ፡ መንፈሴም ፡ አምላኬን
ውርደቴን ፡ ተመልክቷል ፡ የባሪያይቱን
ብርቱ ፡ የሆነው ፡ እርሱ ፡ በእኔ ፡ ክብሩን ፡ ገልጧል
ትዕቢተኛን ፡ አዋርዶ ፡ ትሁቱን ፡ አክብሯል

ቃል ፡ ነበር ፡ ቃልም ፡ እግዚአብሔር
ይህም ፡ ቃል ፡ በአብ ፡ ዘንድ ፡ ነበር
በእርሱ ፡ ሕይወት ፡ ትኖራለች
ሕይወትም ፡ የሰው ፡ ብርሃን ፡ ነች

ከሆነው ፡ አንዳች ፡ አለእርሱ
አልሆነም ፡ ሁሉ ፡ ሆነ ፡ በርሱ
ዓለምን ፡ ያጸናበት ፡ ቃሉ
እነሆ ፡ ለሚያምኑበት ፡ ሁሉ

ቃልም ፡ ሥጋ ፡ ሆነና ፡ ፀጋን ፡ እውነት ፡ ተሞልቶ
በእኛ ፡ ዘንድ ፡ አደረ ፡ ክብሩን ፡ አየን ፡ ጐልቶ
በአባቱ ፡ እቅፍ ፡ ሆኖ ፡ አብን ፡ የተረከው
ቀድሞም ፡ የነበረው ፡ ቃል ፡ ወልድ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው