ነፍሴ (Nefsie) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Azeb Hailu 1.png


(1)

እምቢ
(Embi)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

ከሰማይ ፡ የመጣው ፡ የውዴ ፡ ውብ ፡ ቃል
ልጄ ፡ ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ አንቺ ፡ የኔ ፡ ሲል
በኮረብታዎች ፡ ላይ ፡ መጣልኝ ፡ ሲዘል
ሐዘኔን ፡ ሊያስረሳ ፡ ነፍሴን ፡ ሊያባብል (፪x)

አዝ፦ የነፍሴ ፡ የውስጤ ፡ የልቤ ፡ የሚገባው ፡ ወዳጄ
በቃሉ ፡ መጥቷል ፡ ወደ ፡ ደጄ
ሲያንኳኳ ፡ ከፍቼ ፡ የክብርን ፡ ንጉሥ ፡ አስገባለሁ
በአፉ ፡ ቃል ፡ ነፍሴን ፡ አጠግባለሁ

ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ ተነሽ ፡ ውበቴ ፡ ሆይ ፡ ነይ
ክረምቱም ፡ አለፈ ፡ ብቅ ፡ አትይም ፡ ወይ
አበቦች ፡ በምድር ፡ ይኸው ፡ ተገለጡ
ወይኖችም ፡ አበቡ ፡ መዓዛቸውን ፡ ሰጡ

በዓለት ፡ ንቃቃት ፡ ያለሽ ፡ እርግብ ፡ ሆይ
ጊዜው ፡ ደርሷልና ፡ ነይ ፡ እንተያይ
እያለ ፡ ሲያጽናናኝ ፡ ወዳጄ ፡ በቃሉ
ነፍሴም ፡ ተነቃቃች ፡ እግሮቼም ፡ ዘለሉ

አዝ፦ የነፍሴ ፡ የውስጤ ፡ የልቤ ፡ የሚገባው ፡ ወዳጄ
በቃሉ ፡ መጥቷል ፡ ወደ ፡ ደጄ
ሲያንኳኳ ፡ ከፍቼ ፡ የክብርን ፡ ንጉሥ ፡ አስገባለሁ
በአፉ ፡ ቃል ፡ ነፍሴን ፡ አጠግባለሁ

የሥጋና ፡ የደሜን ፡ የልቤን ፡ ትርታ
የመንፈሴን ፡ ጩኸት ፡ የነፍሴን ፡ ሙግቷ
ከወንድም ፡ አልጦ ፡ እኔን ፡ ሚጠጋጋ
ወዳጅ ፡ አለኝና ፡ ለርሱ ፡ ብቻ ፡ ላውጋ

ዘልቆ ፡ የሚያረሰርስ ፡ ቃል ፡ አለና ፡ ባፉ
ሥሙን ፡ እየጠራሁ ፡ ልግባ ፡ ወደ ፡ እቅፉ
ቃል ፡ ብቻ ፡ ይናገር ፡ እኔም ፡ እሰማለሁ
ሸክሜን ፡ ሲያራግፈው ፡ ያኔ ፡ ሰው ፡ እሆናለሁ

አዝ፦ የነፍሴ ፡ የውስጤ ፡ የልቤ ፡ የሚገባው ፡ ወዳጄ
በቃሉ ፡ መጥቷል ፡ ወደ ፡ ደጄ
ሲያንኳኳ ፡ ከፍቼ ፡ የክብርን ፡ ንጉሥ ፡ አስገባለሁ
በአፉ ፡ ቃል ፡ ነፍሴን ፡ አጠግባለሁ