መገረም (Megerem) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Azeb Hailu 1.png


(1)

እምቢ
(Embi)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

አዝ፦ መገረም ፡ ገብቶበት ፡ ቃል ፡ እንደጠፋዉ
የልቤን ፡ ለመግለጽ ፡ ቋንቋ ፡ እንዳጠረዉ
በአሰራርህ ፡ ነፍሴ ፡ ተደንቃ ፡ ኖራለች
ምሥጋናው ፡ አንሶባት ፡ እንባን ፡ ታፈሳለች

ተባረክ ፡ ትልሃለች
ተመስገን ፡ ትልሃለች
ከፍ ፡ በል ፡ ትልሃለች
ነፍሴ ፡ እጅግ ፡ ወዳሃለች (፪x)

ከገመትኩትና ፡ ካሰብኩት ፡ በላይ
ማዳንህ ፡ ሲገለጥ ፡ ከላይ ፡ ከሰማይ
ሲደራረብብኝ ፡ ቸርነት ፡ ምህረትህ
የምለው ፡ ሲጠፋኝ ፡ አምላኬ ፡ በፊትህ

እንባ ፡ ቋንቋዬ ነው ፡ ይፍሰስ ፡ ከእግርህ ፡ ሥር
ያለኝን ፡ ምሥጋና ፡ ያውጣው ፡ ይናገር
ይገባሃልና ፡ የነፍሴ ፡ ስሜቷ
ባክህ ፡ ዝም ፡ አትበል ፡ ተቀበላት ፡ ጌታ

አዝ፦ መገረም ፡ ገብቶበት ፡ ቃል ፡ እንደጠፋዉ
የልቤን ፡ ለመግለጽ ፡ ቋንቋ ፡ እንዳጠረው
በአሰራርህ ፡ ነፍሴ ፡ ተደንቃ ፡ ኖራለች
ምሥጋናው ፡ አንሶባት ፡ እንባን ፡ ታፈሳለች

ተባረክ ፡ ትልሃለች
ተመስገን ፡ ትልሃለች
ከፍ ፡ በል ፡ ትልሃለች
ነፍሴ ፡ እጅግ ፡ ወዳሃለች (፪x)

እንዲሁ ፡ ተመስገን ፡ ብዬ ፡ የማላልፈው
ደግሞም ፡ በቋንቋዬ ፡ በቃል ፡ የማልገልጸው
በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ከቶ ፡ ማልረሳው
አምላክ ፡ ቸርነትህ ፡ ለኔስ ፡ ብዙ ፡ ነው

አቤት ፡ አሰራርህ ፡ እጅግ ፡ ይደንቀኛል
መናገር ፡ ስጀምር ፡ እንባ ፡ ይቀድመኛል
ለማመስገን ፡ ቋንቋ ፡ ቃል ፡ አጥሮኛልና
በእንባዬ ፡ ላክብርህ ፡ ልውደቅ ፡ ልስገድና

አዝ፦ መገረም ፡ ገብቶበት ፡ ቃል ፡ እንደጠፋዉ
የልቤን ፡ ለመግለጽ ፡ ቋንቋ ፡ እንዳጠረው
በአሰራርህ ፡ ነፍሴ ፡ ተደንቃ ፡ ኖራለች
ምሥጋናው ፡ አንሶባት ፡ እንባን ፡ ታፈሳለች

ተባረክ ፡ ትልሃለች
ተመስገን ፡ ትልሃለች
ከፍ ፡ በል ፡ ትልሃለች
ነፍሴ ፡ እጅግ ፡ ወዳሃለች (፪x)

እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ሆንከኝ ፡ ደስ ፡ ብሎኛል
ከዚህ ፡ በላይ ፡ ባርኮት ፡ ከቶ ፡ የት ፡ ይገኛል
አንተን ፡ ያገኘሁ ፡ ቀን ፡ ቤት ፡ ኑሮዬ ፡ ሞላ
ለዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ተገኘለት ፡ መላ

ምላሽ ፡ ባይሆነኝም ፡ ይህ ፡ የኔ ፡ ምሥጋና
ላደርግ ፡ የምችለው ፡ ይሄንን ፡ ነውና
ስለዚህ ፡ ተባረክ ፡ እላለሁ ፡ ከነፍሴ
የምወድህ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ንጉሤ

አዝ፦ መገረም ፡ ገብቶበት ፡ ቃል ፡ እንደጠፋዉ
የልቤን ፡ ለመግለጽ ፡ ቋንቋ ፡ እንዳጠረው
በአሰራርህ ፡ ነፍሴ ፡ ተደንቃ ፡ ኖራለች
ምሥጋናው ፡ አንሶባት ፡ እንባን ፡ ታፈሳለች

ተባረክ ፡ ትልሃለች
ተመስገን ፡ ትልሃለች
ከፍ ፡ በል ፡ ትልሃለች
ነፍሴ ፡ እጅግ ፡ ወዳሃለች (፪x)