From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
አዜብ ፡ ኃይሉ (Azeb Hailu)
|
|
፩ (1)
|
እምቢ (Embi)
|
ዓ.ም. (Year):
|
፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002)
|
ቁጥር (Track):
|
፯ (7)
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች (Albums by Azeb Hailu)
|
|
አዝ፦ ለጌትነቱ ፡ ወሰን ፡ የለዉ
ይህንን ፡ አምላክ ፡ ማን ፡ ልበለዉ
በምንስ ፡ ቋንቋ ፡ ስለርሱ ፡ ላውራ
ታምራቶቹን ፡ የፍቅሩን ፡ ሥራ (፪x)
(አሃሃሃሃ) ፡ ከምድር ፡ ጫፍ ፡ እስከ ፡ ጫፍ
(አሃሃሃሃ) ፡ እርሱን ፡ ያመልካሉ
(አሃሃሃሃ) ፡ ትዕዛዙን ፡ ይሰማል
(አሃሃሃሃ) ፡ ንፋስ ፡ ማዕበሉ
የሰማይ ፡ ሠራዊት ፡ የሚያውጁለት
በጐነቱንና ፡ የርሱን ፡ ጌትነት (፪x)
አዝ፦ ለጌትነቱ ፡ ወሰን ፡ የለዉ
ይህንን ፡ አምላክ ፡ ማን ፡ ልበለዉ
በምንስ ፡ ቋንቋ ፡ ስለርሱ ፡ ላውራ
ታምራቶቹን ፡ የፍቅሩን ፡ ሥራ (፪x)
(አሃሃሃሃ) ፡ ክብርን ፡ እንዲያወሩ
(አሃሃሃሃ) ፡ ያበጃጀሃቸው
(አሃሃሃሃ) ፡ የሚያሞጋግሱህ
(አሃሃሃሃ) ፡ እንዴት ፡ ብዙ ፡ ናቸው
አእላፋት ፡ በሰማይ ፡ እልፎች ፡ በምድር
ድንቅ ፡ ነህ ፡ ይሉሃል ፡ አንተን ፡ እግዚአብሔር
አእላፋት ፡ በሰማይ ፡ እልፎች ፡ በምድር
ጌታ ፡ ነህ ፡ ይሉሃል ፡ አንተን ፡ እግዚአብሔር
አዝ፦ ለጌትነቱ ፡ ወሰን ፡ የለዉ
ይህንን ፡ አምላክ ፡ ማን ፡ ልበለዉ
በምንስ ፡ ቋንቋ ፡ ስለርሱ ፡ ላውራ
ታምራቶቹን ፡ የፍቅሩን ፡ ሥራ (፪x)
(አሃሃሃሃ) ፡ አፍ ፡ ያለው ፡ የሌለው
(አሃሃሃሃ) ፡ መልእክት ፡ አለኝ ፡ ይላል
(አሃሃሃሃ) ፡ የሰራኝ ፡ እግዚአብሔር
(አሃሃሃሃ) ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ ያወራል
በግራና ፡ በቀኝ ፡ በሁሉም ፡ አቅጣጫ
ፍጥረት ፡ የሚያወራው ፡ ያንተን ፡ ችሎት ፡ ብቻ
በግራና ፡ በቀኝ ፡ በሁሉም ፡ አቅጣጫ
ፍጥረት ፡ የሚያወራው ፡ ያንተን ፡ ስልጣን ፡ ብቻ
አዝ፦ ለጌትነቱ ፡ ወሰን ፡ የለዉ
ይህንን ፡ አምላክ ፡ ማን ፡ ልበለዉ
በምንስ ፡ ቋንቋ ፡ ስለርሱ ፡ ላውራ
ታምራቶቹን ፡ የፍቅሩን ፡ ሥራ (፪x)
|