እቅፍ ፡ ድግፍ (Eqef Degef) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Azeb Hailu 1.png


(1)

እምቢ
(Embi)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:54
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

አዝ፦ እቅፍ ፡ ድግፍ ፡ እቅፍ ፡ በምክሩ ፡ ድግፍ
እቅፍ ፡ ድግፍ ፡ እቅፍ ፡ በቃሉ ፡ ድግፍ
አርጐ ፡ የሚመራ ፡ በዘመናት ፡ መሃል
እየሰባበረ ፡ ቅጥሩን ፡ የሚያዘልል

ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ አሃ
ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ እህ (፪x)

የአባትነት ፡ ፍቅር ፡ ምክሩ : ሳይለየኝ ፡ ማስተማሩ
ልክ ፡ እንደ ፡ ዓይን ፡ ብሌን : ተንከባክቧት ፡ ሕይወቴን (፪x)
እንዳልወድቅ ፡ እንዳልጠፋ : እየሰጠኝ ፡ ተስፋ
ይኸው ፡ አለሁኝ ፡ በቤቱ : እየዘመርኩ ፡ ምህረቱን (፪x)

አዝ፦ እቅፍ ፡ ድግፍ ፡ እቅፍ ፡ በምክሩ ፡ ድግፍ
እቅፍ ፡ ድግፍ ፡ እቅፍ ፡ በቃሉ ፡ ድግፍ
አርጐ ፡ የሚመራ ፡ በዘመናት ፡ መሃል
እየሰባበረ ፡ ቅጥሩን ፡ የሚያዘልል

ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ አሃ
ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ እህ (፪x)

በጉያዎቹ ፡ ሸሽጐ : ከመከራው ፡ ቀን ፡ ታድጐ
ጠላቶቼ ፡ እንደጥላ : ቀሩና ፡ ወደ ፡ ኋላ (፪x)
ያንን ፡ ዘመን ፡ በእርሱ ፡ አልፌ : ከሞት ፡ ወጥመድ ፡ ተርፌ
ከክብር ፡ ጋር ፡ ዛሬን ፡ እንዳይ : ፈቀደልኝ ፡ ከሰማይ (፪x)

አዝ፦ እቅፍ ፡ ድግፍ ፡ እቅፍ ፡ በምክሩ ፡ ድግፍ
እቅፍ ፡ ድግፍ ፡ እቅፍ ፡ በቃሉ ፡ ድግፍ
አርጐ ፡ የሚመራ ፡ በዘመናት ፡ መሃል
እየሰባበረ ፡ ቅጥሩን ፡ የሚያዘልል

ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ አሃ
ማነው ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ እህ (፪x)

በሃሩሩ ፡ በበረሃ : አፍለቅልቆ ፡ ከአለት ፡ ውኃ
የመላእክትን ፡ መና : ከሰማይ ፡ ያወርድና (፪x)
በእሳት ፡ አምድ ፡ በደመና : ከፊት ፡ ፊት ፡ ይመራና
ወደ ፡ ተስፋይቱ ፡ ምድር : ያደርሰኛል ፡ በክብር (፪x)