እምቢ (Embi) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Azeb Hailu 1.png


(1)

እምቢ
(Embi)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

የጀግና ፡ ልጅ ፡ ጀግና ፡ ነኝ ፡ በመስቀል ፡ ጣር ፡ ያፈራኝ
ከሞት ፡ ጋራ ፡ ተወራርዶ ፡ አሸንፎታል ፡ አዋርዶ
የአንበሳ ፡ ልጅ ፡ ነኝ ፡ አንበሳ ፡ ሥሙን ፡ ስመዘው ፡ ሳነሳ
ማንስ ፡ ቀርቦ ፡ ሊደፍረኝ ፡ የኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ እኔ ፡ ነኝ

(እምቢ) ፡ ሕይወት ፡ ይሻለኛል ፡ (እምቢ) ፡ ሰላም ፡ ነፃነት
(እምቢ) ፡ ክብር ፡ እያለልኝ ፡ (እምቢ) ፡ አልሻም ፡ ውርደት
(እምቢ) ፡ ብርሃን ፡ ከፊቴ ፡ (እምቢ) ፡ ደምቆ ፡ እየበራ
(እምቢ) ፡ አልደናበርም ፡ (እምቢ) ፡ በጨለማው ፡ ስፍራ

ሲያምረው ፡ ሽንፈት ፡ ያ ፡ ውርደት ፡ መጥቶ ፡ ነካካኝ ፡ ጥቂት
መች ፡ ልደነግጥ ፡ ልፈራ ፡ አለኝ ፡ ጉልበት ፡ የሚያኮራ
ሥሙን ፡ ጠራሁ ፡ ወነጨፍኩኝ ፡ ወጥመዱንም ፡ ሰባበርኩኝ
መታሰቢያው ፡ ፈጥኖ ፡ ጠፋ ፡ ያዳነኝ ፡ ሥም ፡ ክብሩ ፡ ይስፋ

(እምቢ) ፡ ዳግም ፡ አትገዛኝም ፡ (እምቢ) ፡ ክጄሃለሁ ፡ በቃ
(እምቢ) ፡ አልጭበረበርም ፡ (እምቢ) ፡ ሙት ፡ መንፈሴ ፡ ነቃ
(እምቢ) ፡ እግሬን ፡ አቅንቻለሁ ፡ (እምቢ) ፡ ላልል ፡ ወደ ፡ ኋላ
(እምቢ) ፡ የሰማይ ፡ ብርሃን ፡ (እምቢ) ፡ እኔነቴን ፡ ሞላ

ልሰግድለት ፡ እንዳመልከው ፡ ምስሉን ፡ ሰርቶ ፡ ፊቴ ፡ አቆመው
ውደቂለት ፡ ተንበርከኪ ፡ የወርቁን ፡ ምስል ፡ አምልኪ
ባልሰግድለት ፡ ባላደርገው ፡ በእቶን ፡ እሳት ፡ መጣል ፡ ነው
በዚያ ፡ መጣልን ፡ እመርጣለሁ ፡ የእርሱን ፡ ምስል ፡ ከማመልከው [1]

(እምቢ) ፡ የሚሰገድለት ፡ (እምቢ) ፡ እያለኝ ፡ አምላክ
(እምቢ) ፡ ለአሕዛብ ፡ አማልክት ፡ (እምቢ) ፡ አልንበረከክ
(እምቢ) ፡ ሲያምረው ፡ ይቅር ፡ እንጂ ፡ (እምቢ) ፡ የኔ ፡ ዜማ ፡ እልልታ
(እምቢ) ፡ እርሱ ፡ ለአምላኬ ፡ ነው ፡ (እምቢ) ፡ ለጌቶቹ ፡ ጌታ

ነይ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ነይ ፡ እያለ ፡ በቁልምጫ ፡ እያባበለ
ሊማርከኝ ፡ ብዙ ፡ ጣረ ፡ ግን ፡ አልሆነለት ፡ ከሰረ
ላዩ ፡ መስሎ ፡ እንዳበባ ፡ ውስጡ ፡ እሬት ፡ ነው ፡ ጨለማ
ኋላ ፡ ጠልፎ ፡ ከሚጥለኝ ፡ እምቢ ፡ ብያለሁ ፡ ይቅርብኝ

(እምቢ) ፡ የዓለምን ፡ ጥሪ ፡ (እምቢ) ፡ የዓለምን ፡ ግብዣ
(እምቢ) ፡ ከቶ ፡ አንገናኝም ፡ (እምቢ) ፡ እስከመጨረሻ
(እምቢ) ፡ እግዚአብሔርን ፡ መፍራት ፡ (እምቢ) ፡ ያዋጣኛልና
(እምቢ) ፡ እጅ ፡ አልሰጥም ፡ ለዓለም ፡ (እምቢ) ፡ ሞት ፡ አለበትና

  1. ዳንኤል ፫ (Daniel 3)