ደስ ፡ የሚለኝ (Des Yemilegn) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Azeb Hailu 1.png


(1)

እምቢ
(Embi)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

አዝ፦ደስ ፡ የሚለኝ ፡ ያኔ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ያኔ
ስትከብር ፡ ስትነግስልኝ ፡ ምድህኔ
የምረካው ፡ ያኔ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ያኔ
ከፍ ፡ ስትል ፡ ስትገንልኝ ፡ መድህኔ

ክብርህን ፡ ሳይ ፡ እጠግባለሁ
በምስጋናህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
አንተን ፡ ማክበር ፡ ማሞጋገስ ፡ ያረካኛል (፪x)

ክበርልኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ ክበርልኝ (፫x)
ንገሥልኝ ፡ የኔ ፡ ወዳጅ ፡ ንገሥልኝ (፫x)

ሰው ፡ ሁሉ ፡ ገብቶት ፡ ሲያመሰግንህ
አምላኬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ጌታዬም ፡ ሲልህ
ሲዘመር ፡ ላንተ ፡ ሲሆን ፡ እልልታ
በሁሉም ፡ ስፍራ ፡ ስትሆን ፡ ጌታ

ያኔ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ደስታ ፡ ስትነግሥልኝ ፡ ጌታ (፪x)
ያኔ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ደስታ ፡ ስትከብርልኝ ፡ ጌታ (፪x)

አዝ፦ደስ ፡ የሚለኝ ፡ ያኔ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ያኔ
ስትከብር ፡ ስትነግስልኝ ፡ ምድህኔ
የምረካው ፡ ያኔ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ያኔ
ከፍ ፡ ስትል ፡ ስትገንልኝ ፡ መድህኔ

ክብርህን ፡ ሳይ ፡ እጠግባለሁ
በምስጋናህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
አንተን ፡ ማክበር ፡ ማሞጋገስ ፡ ያረካኛል (፪x)

ክበርልኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ ክበርልኝ (፫x)
ንገስልኝ ፡ የኔ ፡ ወዳጅ ፡ ንገሥልኝ (፫x)

ሰው ፡ በፈቃዱ ፡ ሳይገደድ
ጌታን ፡ ሲከተል ፡ እርሱን ፡ ሲወድ
በቤቱም ፡ ሲኖር ፡ ሲቀር ፡ ተማርኮ
በፍቅሩ ፡ ጉልበት ፡ ሳይ ፡ ተንበርክኮ

ያኔ ፡ ነው ፡ ደስታዬኮ ፡ ሲበዛልህ ፡ አምልኮ (፬x)

አዝ፦ደስ ፡ የሚለኝ ፡ ያኔ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ያኔ
ስትከብር ፡ ስትነግስልኝ ፡ ምድህኔ
የምረካው ፡ ያኔ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ያኔ
ከፍ ፡ ስትል ፡ ስትገንልኝ ፡ መድህኔ

ክብርህን ፡ ሳይ ፡ እጠግባለሁ
በምስጋናህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
አንተን ፡ ማክበር ፡ ማሞጋገስ ፡ ያረካኛል (፪x)

ክበርልኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ ክበርልኝ (፫x)
ንገስልኝ ፡ የኔ ፡ ወዳጅ ፡ ንገሥልኝ (፫x)

ፍጥረትም ፡ ካንተ ፡ ሥር ፡ ካንተ ፡ በታች
ሲሆን ፡ ሲገዛ ፡ ደግሞም ፡ ሲመች
በሥልጣንህ ፡ ቃል ፡ ታዞ ፡ ሲመራ
የገነነውን ፡ ስምህን ፡ ሲፈራ

ያኔ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ደስታ ፡ ስትነግሥልኝ ፡ ጌታ (፪x)
ያኔ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ደስታ ፡ ስትከብርልኝ ፡ ጌታ (፪x)

አዝ፦ደስ ፡ የሚለኝ ፡ ያኔ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ያኔ
ስትከብር ፡ ስትነግስልኝ ፡ ምድህኔ
የምረካው ፡ ያኔ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ያኔ
ከፍ ፡ ስትል ፡ ስትገንልኝ ፡ መድህኔ

ክብርህን ፡ ሳይ ፡ እጠግባለሁ
በምስጋናህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል
አንተን ፡ ማክበር ፡ ማሞጋገስ ፡ ያረካኛል (፪x)

ክበርልኝ ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ ክበርልኝ (፫x)
ንገስልኝ ፡ የኔ ፡ ወዳጅ ፡ ንገሥልኝ (፫x)