በግራና ፡ በቀኝ (Begrana Beqegn) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Azeb Hailu 1.png

(1)

እምቢ
(Embi)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002)
ቁጥር (Track):

(5)

ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

በግራና ፡ በቀኜ ፡ ሆናችሁ
ልታጠምዱኝ ፡ ያሰፈሰፋችሁ
በሉ ፡ ስሙኝ ፡ እስቲ ፡ ልንገራችሁ
በእኔ ፡ ዘንድ ፡ ደግሞ ፡ ምን ፡ ቀራችሁ

አትጠጉኝ ፡ አትነካኩኝ
ተለያየን ፡ እኔ ፡ የጌታ ፡ ነኝ
በዓለም ፡ ብኖር ፡ አይደለሁ ፡ የዓለም
መኖሪያዬ ፡ ለዘልዓለም

በዚህች ፡ ምድር ፡ ፍጹም ፡ አይደለም
በዚህች ፡ ዓለም ፡ ፍጹም ፡ አይደለም (፪x)

አዝ፦ (አሃ) ፡ ዓይኖቼን ፡ አንስቼ ፡ (አሃ) ፡ ሳይ ፡ ወደ ፡ ሰማይ
(አሃ) ፡ በአብ ፡ ቤት ፡ ቁጭ ፡ ያለው ፡ (አሃ) ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ
(አሃ) ፡ ተስፋውን ፡ የሰጠኝ ፡ (አሃ) ፡ መጥቶ ፡ ሊወስደኝ
(አሃ) ፡ የዘላለም ፡ አባት ፡ (አሃ) ፡ ኢየሱስ ፡ አለኝ

የአምላክ ፡ ምክር ፡ የልዑል ፡ ትምህርቱ
የሰማሁት ፡ አዋጅ ፡ የመንግሥቱ
ውስጤ ፡ ገብቶ ፡ ሰርፆ ፡ ልቦናዬ
አጣብቆኛል ፡ ከውዱ ፡ ጌታዬ

ጊዜም ፡ የለኝ ፡ ዓለም ፡ ምሰማሽ
እረሳሁሽ ፡ አንቺም ፡ እኔን ፡ እርሺኝ
በአምላኬ ፡ ዘንድ ፡ ተሰራልኝ ፡ ቤቴ
ሰማያዊ ፡ ሆኗል ፡ ዜግነቴ (፭x)

አዝ፦ (አሃ) ፡ ዓይኖቼን ፡ አንስቼ ፡ (አሃ) ፡ ሳይ ፡ ወደ ፡ ሰማይ
(አሃ) ፡ በአብ ፡ ቤት ፡ ቁጭ ፡ ያለው ፡ (አሃ) ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ
(አሃ) ፡ ተስፋውን ፡ የሰጠኝ ፡ (አሃ) ፡ መጥቶ ፡ ሊወስደኝ
(አሃ) ፡ የዘላለም ፡ አባት ፡ (አሃ) ፡ ኢየሱስ ፡ አለኝ

በዚህ ፡ ምድር ፡ ቋሚ ፡ ነገር ፡ የለም
ምስቅልቅል ፡ ነው ፡ ሲኖር ፡ በዚህ ፡ ዓለም
የከበረ ፡ ነገ ፡ ይዋረዳል
ያለቀሰ ፡ በተራው ፡ ይስቃል

ግራ ፡ ገብቶት ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲሰጋ
የማምለጫው ፡ መንገዱ ፡ ሲዘጋ
ጌታዬና ፡ አምላኬ ፡ ነህ ፡ ብዬው
የእንግድነት ፡ ኑሮ ፡ ጀምሬያለሁ

አገር ፡ አለኝ ፡ ቤቴ ፡ በሰማይ ፡ ነው
ተስፋ ፡ አለኝ ፡ ርስቴ ፡ በሰማይ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ (አሃ) ፡ ዓይኖቼን ፡ አንስቼ ፡ (አሃ) ፡ ሳይ ፡ ወደ ፡ ሰማይ
(አሃ) ፡ በአብ ፡ ቤት ፡ ቁጭ ፡ ያለው ፡ (አሃ) ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ
(አሃ) ፡ ተስፋውን ፡ የሰጠኝ ፡ (አሃ) ፡ መጥቶ ፡ ሊወስደኝ
(አሃ) ፡ የዘላለም ፡ አባት ፡ (አሃ) ፡ ኢየሱስ ፡ አለኝ

የሰው ፡ ዕድሜ ፡ መች ፡ ከሰባው ፡ ያልፋል
ቢበረታ ፡ ሰማንያ ፡ ይሆናል
ጥቂት ፡ ታይቶ ፡ ኋላ ፡ እንደሚጠፋ
እንፋሎት ፡ ነው ፡ የኛ ፡ መኖር ፡ ተስፋ

እኔ ፡ ግን ፡ መች ፡ በምድር ፡ እቀራለሁ
በሰማይ ፡ ቤት ፡ መኖሪያ ፡ አግኝቻለሁ
ጌታ ፡ የግል ፡ አዳኜ ፡ ሆኖኛል
በብርሃኑ ፡ ብርሃን ፡ ወጥቶልኛል

የዘላለም ፡ ሕይወት ፡ ተሰጥቶኛል
የፍርድ ፡ ቀን ፡ ለምን ፡ ያሰጋኛል (፪x)

አዝ፦ (አሃ) ፡ ዓይኖቼን ፡ አንስቼ ፡ (አሃ) ፡ ሳይ ፡ ወደ ፡ ሰማይ
(አሃ) ፡ በአብ ፡ ቤት ፡ ቁጭ ፡ ያለው ፡ (አሃ) ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ
(አሃ) ፡ ተስፋውን ፡ የሰጠኝ ፡ (አሃ) ፡ መጥቶ ፡ ሊወስደኝ
(አሃ) ፡ የዘላለም ፡ አባት ፡ (አሃ) ፡ ኢየሱስ ፡ አለኝ