የሰማይ ፡ ወፎች (Yesemay Wefoch) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(5)

መጀመሪያ
(መጀመሪያ)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:32
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

የሰማይ ወፎች መጋቢ
የምድር አበቦች አልባሽ
በደሙ የዋጀኝ እኔን
አይዘነጋኝም ጭራሽ X2
ለኔ ከነሱ በላይ ለኔ ይራራልኛል
የምን ውሃ ና እንጀራ ነፍሱን ሰውቶልኛል
ይወደኛል X2

አዝ፥ ስለዚህ ለምን እፈራለው ስለዚህ ለምን ሰጋለው ስለዚህ ለምን አዝናለው
    በምንም አልጨነቅም በምንም አልታወክም
    የሰማይ አባት ምን እንድያስፈልገኝ ያውቃል ይሰጠኛል X2

በእምነት ደጁን አንኳኳለሁ መሻቴን እለምንሀለሁ
በጎውን ፈቃዱም በህይወቴ እንደሚሠራው አምናለሁ X2
አሳን ለሚሻ እባብ ዳቦ ለሚል ድንጋይ
አይሰጠውም የኔ አባት ያለ የሚኖር ሰማዩ ኤልሻዳይ X2

አዝ፥ ስለዚህ ለምን እፈራለው ስለዚህ ለምን ሰጋለው ስለዚህ ለምን አዝናለው
    በምንም አልጨነቅም በምንም አልታወክም
    የሰማይ አባት ምን እንድያስፈልገኝ ያውቃል ይሰጠኛል X2