From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ባይሆን ኖሮ እግዚአብሔር ከኔ ጋር
ባይጋርደኝ ቅጥርን ባይቀጥር(፪)
ጠላቶቼ በቁጣቸው ብዛት
ህያው ሳለሁ በዋጡኝም ነበር(፪)
ግን እግዚአብሔር ምህረትን አበዛ
አሻገረኝ መንገድ አበጀና (፪)
ይኸው ዛሬ በህይወት ቆሚያለሁ
በብዙ ድል በብዙ ምስጋና (፪)
ተጠነቀቀልኝ ጌታዬ ተጠነቀቀልኝ
ተጠነቀቀልኝ አምላኬ ተጠነቀቀልኝ(፪)
ንብ ማር እንደሚከብ ከበቡ በጭካኔ መንፈስ አየሉ
ከጃቸው ሚያስጥል እንደሌለ እጅግ የበረቱ መሰሉ
አላስተዋሉትም ነበረ ከኔ ጋር ያለውን እረኛ
ድካም ከቶ እንደማያውቀው እኔን ለማዳን እንደማይተኛ
ስላለ ግን ጌታ ከጎኔ ስላል እርሱ ካጠገቤ
በጠላቴ ፉከራ ዛቻ ስጋት አይገባውም ይህ ልቤ
ተማምኜ በርሱ ተማምኜ በትከሻው መሃል አድራለሁ
ዘላለም በክንፎቹ ጥላ በሰላም በደስታ ኖራለሁ
ሰላም ነው ሁሉ ሰላም ነዉ
ጌታ ነው ከጎኔ ያለዉ
ደህና ነው ሁሉ ደህና ነዉ
ጌታ ነው በቤቴ ያለዉ
የላባ ቀንበር ቢከብደበት በቸገር ቢጠማ ቢከፋ
አመልጣለሁ ብሎ ቢያስብም ማልዶ ቢኮበልል ቢጠፋ
ተከታተለዉ ደረሰበት በቁጣው ሊያጠፋውም ዝቶ
የወደደውንም እንዲያደርግ በእጁ በሃይሉ ተመክቶ
የያቆብ አምላክ ቀደመ ለላባ በህልም ነገረው
እንክዋን ልትጎዳ ልታጠፋው በክፉ ቃል አትናገረው
በማስጠንቀቂያ ቃል ገስጾ ሃሳብ እቅዱን አፈረሰ
ያሳዳጁን ዛቻ ላልሰማው ለባሪያው ለያቆብ ደረሰ
ሰላም ነው ሁሉ ሰላም ነዉ
ጌታ ነው ከጎኔ ያለዉ
ደህና ነው ሁሉ ደህና ነዉ
ጌታ ነው በቤቴ ያለዉ
ባይሆን ኖሮ እግዚአብሔር ከኔ ጋር
ባይጋርደኝ ቅጥርን ባይቀጥር(፪)
ጠላቶቼ በቁጣቸው ብዛት
ህያው ሳለሁ በዋጡኝም ነበር(፪)
ግን እግዚአብሔር ምህረትን አበዛ
አሻገረኝ መንገድ አበጀና (፪)
ይኸው ዛሬ በህይወት ቆሚያለሁ
በብዙ ድል በብዙ ምስጋና (፪)
ተጠነቀቀልኝ ጌታዬ ተጠነቀቀልኝ
ተጠነቀቀልኝ አምላኬ ተጠነቀቀልኝ(፪)
እግዚአብሔር ብርሃኔ ነው ለኔ ጨለማው መንገዴን እንዳይዘጋ
ፍርሃት ስጋት ሁሉ ቀረ በልጁ ወደርሱ ስጠጋ
ተሰነካክዬ እንዳልቀር ህይወቴም እንዳትሆን ከንቱ
እንዳልሆንበት መሳለቂያ ገነነልኝ ለኔስ ምህረቱ
ስላለ ግን ጌታ ከጎኔ ስላል እርሱ ካጠገቤ
በጠላቴ ፉከራ ዛቻ ስጋት አይገባውም ይህ ልቤ
ተማምኜ በርሱ ተማምኜ በትከሻው መሃል አድራለሁ
ዘላለም በክንፎቹ ጥላ በሰላም በደስታ ኖራለሁ (፱)
|