መድህኔ (Medhene) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(5)

በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር
(Bemejemeria Egziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 7:07
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

ኢየሱስ ፡ መድህኔ
የተጎሳቆለልኝ ፡ ለኔ
ነፍሴን ፡ ሊያድናት
እርሱ ፡ ሆነ ፡ መስዋእት (፪x)

ደሙ ፡ ያድናል ፡ ደሙ (፫)
የመስቀል ፡ ላይ ፡ ጣሩ ፡ ስቃዩ ፡ ህመሙ

ልከፍልው ፡ በማልችልው ፡ እዳ
በሞት ፡ ጥሪ ፡ ነፍሴ ፡ ተገዳ
ሳዘግም ፡ ወደ ፡ ሲኦል ፡ መንገድ
ከሰማይ ፡ ራርቶልኝ ፡ እግዚአብሔ
ውድና ፡ አንድ ፡ ልጁን ፡ ላከልኝ
በኔ ፡ ፈንታ ፡ እንዲታረድልኝ
ሳያቅማማ ፡ መጣ ፡ ኢየሱሴ
አመለጠች ፡ ከሲኦል ፡ ነፍሴ

አለብኝ ፡ ውለታዉ (፪)የሱስ ፡ የከፈለዉ
ብር ፡ ወርቅ ፡ አይደለም ፡ ነፍሱን ፡ ነዉ(፪x)

ተጠምቶ ፡ ሲጠጣ ፡ መራራ
ሲከፍል ፡ የኔን ፡ ስቃይ ፡ መከራ
የሾህ ፡ አክሊል ፡ ጭኖ ፡ በራሱ
ሲጨነቅ ፡ እስክታልፍ ፡ ነፍሱ
ቀና ፡ ብሎ ፡ ሲያይ ፡ ወደ አባቱ
ጨክኖ ፡ አዞረበት ፡ ፊቱን
አንገቱን ፡ ደፍቶ ፡ ስለእኔ
ተፈጸመ ፡ አለ ፡ መድህኔ

ኢየሱስ ፡ መድህኔ
የተጎሳቆለልኝ ፡ ለኔ
ነፍሴን ፡ ሊያድናት
እርሱ ፡ ሆነ ፡ መስዋእት (፪x)

ደሙ ፡ ያድናል ፡ ደሙ (፫)
የመስቀል ፡ ላይ ፡ ጣሩ ፡ ስቃዩ ፡ ህመሙ

ስለምን ፡ ይሆን ፡ ይሄ ፡ ጌታ
ያጣጣረው ፡ በዚያ ፡ ጎልጎታ
የተሰደበ ፡ የተተፋበት
ባልሰራው ፡ ባልፈጸመው ፡ ሃጢያት
ለካ ፡ ስለ እኔ ፡ ነው ፡ ቤዛ
ነፍሱን ፡ ከፍሎ ፡ ነፍሴን ፡ የገዛ
ቃል ፡ የማይገልጸው ፡ ድንቅ ፡ ፍቅሩ
ገለጠልኝ ፡ በመስቀል ፡ ጣሩ

አለብኝ ፡ ውለታዉ (፪)የሱስ ፡ የከፈለዉ
ብር ፡ ወርቅ ፡ አይደለም ፡ ነፍሱን ፡ ነዉ(፪x)