From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በስግደት ፡ በአምልኮ ፡ በብዙ ፡ ምሥጋና ፡
በዕውነት ፡ በመንፈስ ፡ ፊትህ ፡ ልምጣና ፡
ላምልክህ ፡ እንደገና (፫)
እንደወራጅ ፡ ዉሃ ፡ ልክ ፡ እንደጅረቱ
አይቋረጥብህ ፡ አምልኮዬ ፡ ፊቱ
ይፍሰስ ፡ በማለዳው ፡ ይፍሰስ ፡ በሌሊቱ
መሳይ ፡ ስለሌለው ፡ ጌታ ፡ ጌትነቱ (፪)
ላምልከው ፡ በአምልኮዬ ፡
ላክብረው ፡ በዝማሬዬ
ላግንነው ፡ በዕልልታዬ ፡
ላድምቀው ፡ በጭብጨባዬ
ይገባዋል ፡ እና ፡ ጌታዬ (፬)
የመውደዴን ፡ ልኩን ፡ የፍቅሬን ፡ መግልጫ
ካለኝ ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ የምሰጠው ፡ ብልጫ
ለሕይወቴ ፡ ጌታ ፡ ለነፍሴ ፡ ንጉሥ
አለኝ ፡ የምሰዋው ፡ ከነፍሴ ፡ የሚፈስ
የቅኔው ፡ የዜማ ፡ ሽታ ፡ ታጅቦ ፡ በብዙ ፡ ሆታ
ከምድር ፡ ይውጣ ፡ ያስተጋባ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ማደሪያ ፡ ይግባ
ይገባሃል ፡ እና ፡ ጌታዬ (፬)
በስግደት ፡ በአምልኮ ፡ በብዙ ፡ ምሥጋና ፡
በዕውነት ፡ በመንፈስ ፡ ፊትህ ፡ ልምጣና ፡
ላምልክህ ፡ እንደገና (፫)
|