በስምህ ፡ ውስጥ (Besemhe Wist) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(5)

በመጀመሪያ ፡ እግዚአብሔር
(Bemejemeria Egziabhier)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፱ (2017)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 6:22
ጸሐፊ (Writer):
(Meron Tessema
Property "Writer" has been marked for restricted use.
)
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

በስምህ ውስጥ ሃይል አለ
በስምህ ውስጥ ሞገስ
በስምህ ውስጥ ድል አለ
በስምህ ውስጥ ፈውስ

የጸና ግምብ ነው ስምህ የጻድቅ መሸሻ
ከዚህ ዓለም ግብግብ መሸሸጊያ ዋሻ
ከድካም ህመሜ የምፈወስበት
ኢየሱስ ያንተ ስም መድሃኒት አለበት

ኢየሱስ ኢየሱስ እግዚአብሄር አባት ከፍ ያደረገው ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ በምድር በሰማይ ከፍከፍ ያለ ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ የዲያብሎስን ቀንበር ሰባሪ ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ በጨለማው ላይ ብርሃን አብሪ ስም አለህ

ስምህ ማንነትህ ማንነትህ ስምህ
እንደተጠራህበት እንደዚያው መሆንህ
አዳኝ ሲሉህ አዳኝ ነህ ህይወት ሲሉህ ህይወት
ኢየሱስ ያንተ ስም እውነተኛ እውነት

ኢየሱስ ኢየሱስ እግዚአብሄር አባት ከፍ ያደረገው ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ በምድር በሰማይ ከፍከፍ ያለ ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ የዲያብሎስን ቀንበር ሰባሪ ስም አለህ
ኢየሱስ ኢየሱስ በጨለማው ላይ ብርሃን አብሪ ስም አለህ

በሰልፉ ሜዳ ላይ በውጊያው መንደር
ስምህ የጦር እቃችን የማይበገር
የልጆችህ አንገት ቀና የሚልበት
ኢየሱስ ያንተ ስም ታላቅ ሃይል አለበት