From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ አሃ ፡ አሃሃ ፡ ያኔ ፡ እንደወደደኝ
አሃ ፡ አሃሃ ፡ ዛሬም ፡ ይወደኛል
አሃ ፡ አሃሃ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ፍቅሩ
አሃ ፡ አሃሃ ፡ መች ፡ ቀንሶ ፡ ያውቃል
አሃሃ ፡ እርሱ ፡ ያው ፡ ነው ፡ አልተለዋወጠም
አሃሃ ፡ ምህረቱ ፡ ዛሬም ፡ አልጐደለም
አሃሃ ፡ እርሱ ፡ ያው ፡ ነው ፡ አልተቀያየረም
አሃሃ ፡ ቸርነቱ ፡ ዛሬም ፡ አልጐደለም
ያኔ ፡ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ኤሎሂ ፡ ያለላት
ከሲዖል ፡ እንድትድን ፡ ወዶ ፡ የተሟገተላት
ሞቶ ፡ እስከሚቀበር ፡ ድረስ ፡ የወደዳት ፡ ነፍሴ
ትገዛለታለች ፡ ዛሬም ፡ እያለች ፡ ንጉሤ
ወዶኛልና ፡ አዳነኝ
እያለች ፡ ቅኔ ፡ ስትቀኝ
ላልተለወጠው ፡ ማንነትህ
ምሥጋናም ፡ አላት ፡ ለምህረትህ (፪x)
አዝ፦ አሃ ፡ አሃሃ ፡ ያኔ ፡ እንደወደደኝ
አሃ ፡ አሃሃ ፡ ዛሬም ፡ ይወደኛል
አሃ ፡ አሃሃ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ፍቅሩ
አሃ ፡ አሃሃ ፡ መች ፡ ቀንሶ ፡ ያውቃል
አሃሃ ፡ እርሱ ፡ ያው ፡ ነው ፡ አልተለዋወጠም
አሃሃ ፡ ምህረቱ ፡ ዛሬም ፡ አልጐደለም
አሃሃ ፡ እርሱ ፡ ያው ፡ ነው ፡ አልተቀያየረም
አሃሃ ፡ ቸርነቱ ፡ ዛሬም ፡ አልጐደለም
በሕይወቴ ፡ ውጣ ፡ ውረድ ፡ ባልፍም ፡ በመከራ
እርሱ ፡ ፈፅሞ ፡ አልተወኝም ፡ አለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ
ዓመት ፡ ዘመን ፡ ቢለዋወጥ ፡ ቀንም ፡ በቀን ፡ ላይ
እንከን ፡ አላየሁበትም ፡ ውዴም ፡ ፍቅሩ ፡ ላይ
በምህረቱ ፡ ባለጠጋ
ሆኖ ፡ አየሁ ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ስጠጋ
አይጨምርም ፡ አይቀንስ ፡ ፍቅሩ
እርሱ ፡ ያው ፡ ነው ፡ በዘመኑ (፪x)
አዝ፦ አሃ ፡ አሃሃ ፡ ያኔ ፡ እንደወደደኝ
አሃ ፡ አሃሃ ፡ ዛሬም ፡ ይወደኛል
አሃ ፡ አሃሃ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ፍቅሩ
አሃ ፡ አሃሃ ፡ መች ፡ ቀንሶ ፡ ያውቃል
አሃሃ ፡ እርሱ ፡ ያው ፡ ነው ፡ አልተለዋወጠም
አሃሃ ፡ ምህረቱ ፡ ዛሬም ፡ አልጐደለም
አሃሃ ፡ እርሱ ፡ ያው ፡ ነው ፡ አልተቀያየረም
አሃሃ ፡ ቸርነቱ ፡ ዛሬም ፡ አልጐደለም
የመልካምነቱን ፡ ብዛት ፡ ማን ፡ ቆጥሮ ፡ ይዘልቃል
ከሰማያት ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ነው ፡ ከሲዖል ፡ ይጠልቃል
ማነው ፡ ወዳጅ ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ ከቶ ፡ በዓለም ፡ ላይ
እንኳን ፡ ከሰው ፡ ከዚች ፡ በምድር ፡ የለም ፡ በሰማይ
ወዶኛልና ፡ አዳነኝ
እያልኩኝ ፡ ቅኔው ፡ ስቀኝ
ላልተለወጠው ፡ ማንነትህ
ምሥጋናም ፡ አለኝ ፡ ለምህረትህ (፪x)
አዝ፦ አሃ ፡ አሃሃ ፡ ያኔ ፡ እንደወደደኝ
አሃ ፡ አሃሃ ፡ ዛሬም ፡ ይወደኛል
አሃ ፡ አሃሃ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ፍቅሩ
አሃ ፡ አሃሃ ፡ መች ፡ ቀንሶ ፡ ያውቃል
አሃሃ ፡ እርሱ ፡ ያው ፡ ነው ፡ አልተለዋወጠም
አሃሃ ፡ ምህረቱ ፡ ዛሬም ፡ አልጐደለም
አሃሃ ፡ እርሱ ፡ ያው ፡ ነው ፡ አልተቀያየረም
አሃሃ ፡ ቸርነቱ ፡ ዛሬም ፡ አልጐደለም
|