የሕይወቴ ፡ መመሪያ (Yehiwotie Memeriya) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(2)

አሸናፊ ፡ ነኝ
(Ashenafi Negn)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 5:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

አዝ፦ ማለዳ ፡ አግኝቼው ፡ ቀን ፡ ይናፍቀኛል
ቀትር ፡ ላይ ፡ አይቼው ፡ ምሽት ፡ ይርበኛል
የሕይወቴ ፡ መመሪያ ፡ ፅኑ ፡ መሠረቴ
ትለዋለች ፡ ነፍሴ ፡ ቃልህ ፡ ቁርስ ፡ እራቴ (፪x)

ባነበብኩት ፡ ቁጥር ፡ ባሰላሰልኩት
በዝቶ ፡ ይበራልኛል ፡ የቃልህ ፡ እውነት
ያኔ ፡ ደግሞ ፡ ነፍሴ ፡ ትረሰርሳለች
የምድሩን ፡ ረስታ ፡ ወደላይ ፡ ታያለች

አሁንም ፡ አሁንም ፡ ስትሻህ ፡ ደጋግማ
ልክ ፡ እንደ ፡ ዋላዋ ፡ ቃልህን ፡ ስትጠማ
ቢገባት ፡ ነው ፡ ነፍሴ ፡ የቃልህ፡ ውበቱ
ጠንካራውን ፡ ልቤን ፡ ማሸነፍ ፡ መርታቱ

ተማርኪያለሁ ፡ በቃልህ ፡ ውበት ፡ ተስቢያለሁ
ተማርኪያለሁ ፡ ሕይወቴን ፡ ለእርሱ ፡ ሰጥቻለሁ
ተማርኪያለሁ ፡ በቃልህ ፡ ፍቅር ፡ ተይዣለሁ
ተማርኪያለሁ ፡ ቶሎ ፡ ቶሎ ፡ ፈልገዋለሁ

እየኮረኮረ ፡ ገብቶ ፡ ወደ ፡ ሕይወቴ
ለውጦ ፡ አስቀረው ፡ የውስጥ ፡ ማንነቴን
ልቤም ፡ ተሸነፈ ፡ ተረታ ፡ በቃልህ
አምሮ ፡ ተሸላልሞ ፡ ማደሪያህ ፡ ሆነልህ

እንዳንበረከከው ፡ ግዛው ፡ ሠልጥንበት
በሁለንተናዬ ፡ አንተው ፡ ንገሥበት
ይንቆርቆር ፡ በልቤ ፡ ምክር ፡ ተግሳፅህ
ሲነጋም ፡ ሲመሽም ፡ ምን ፡ ጊዜም ፡ ልስማህ

አዝ፦ ማለዳ ፡ አግኝቼው ፡ ቀን ፡ ይናፍቀኛል
ቀትር ፡ ላይ ፡ አይቼው ፡ ምሽት ፡ ይርበኛል
የሕይወቴ ፡ መመሪያ ፡ ፅኑ ፡ መሠረቴ
ትለዋለች ፡ ነፍሴ ፡ ቃልህ ፡ ቁርስ ፡ እራቴ (፪x)

መንፈሴም ፡ ታደሰ ፡ ውስጤ ፡ በረታታ
ሲለቀቅ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ቃልህ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
ከዓይኔ ፡ ላይ ፡ ተነሳ ፡ ቅርፊቱም ፡ ወደቀ
የሕይወቴም ፡ ብርሃን ፡ በቃልህ ፡ ደመቀ

ዛሬም ፡ አዲስ ፡ ነገም ፡ ሁሌም ፡ ነው ፡ አዲስ
ሲገለጥ ፡ እውነትህ ፡ ለልብ ፡ ለመንፈስ
እውነትም ፡ የሕይወት ፡ ቃል ፡ ነህ ፡ መድኃኒቴ
አረፈች ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ተጣብቃ ፡ ሕይወቴ

ተማርኪያለሁ ፡ በቃልህ ፡ ውበት ፡ ተስቢያለሁ
ተማርኪያለሁ ፡ ሕይወቴን ፡ ለእርሱ ፡ ሰጥቻለሁ
ተማርኪያለሁ ፡ በቃልህ ፡ ፍቅር ፡ ተይዣለሁ
ተማርኪያለሁ ፡ ቶሎ ፡ ቶሎ ፡ ፈልገዋለሁ