የጌታ ፡ ስራ (Yegieta Sera) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(2)

አሸናፊ ፡ ነኝ
(Ashenafi Negn)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

የቱ ፡ ተነግሮ ፡ የቱ ፡ ይተዋል
የጌታ ፡ ሥራ ፡ እጅጉን ፡ በዝቷል
ከየት ፡ አንስቼ ፡ ስንቱን ፡ ላስታውስ
በየማለዳ ፡ ሁልጊዜ ፡ አዲስ

ነግሮ ፡ ሊጨርስ ፡ ማነው ፡ የቻለ
ተዓምራቶቹን ፡ እያስተዋለ
የጌታን ፡ ክብር ፡ ታላቅነቱን
የፍቅሩን ፡ ብዛት ፡ ደግሞ ፡ ጥልቀቱን

ከመታወቅም ፡ ሁሉ ፡ ያለፈ
ከህሊናችን ፡ ሞልቶ ፡ የተረፈ
ነውና ፡ ታላቅ ፡ ሥራው ፡ ብዙ
ለዚህ ፡ ለጌታ ፡ ምሥጋናውን ፡ አብዙ

ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ፍጥረት ፡ የሚያመሰግንህ
ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ክብር ፡ ለአንተ ፡ የተገባ
ስለሆንክ ፡ ገዢ ፡ ብርቱና ፡ ገናና
አሁንም ፡ አሁንም ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና

ፍጥረታት ፡ በሙሉ ፡ በግዛትህ ፡ ናቸው
ስለዚህም ፡ በአንተ ፡ ብዙ ፡ ደስታ ፡ አላቸው
በራሳቸው ፡ ቋንቋ ፡ ይመሰክራሉ
የእግዚአብሔር ፡ ሥራ ፡ ፍጥረት ፡ ነን ፡ እያሉ ፡ ሃሌሉያ

የለህም ፡ መሳይ (፫x) ፡ በምድር ፡ በሰማይ
የለህም ፡ እኩያ (፫x) ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ

በደማቅ ፡ ብርሃን ፡ እራስክን ፡ ሰውረህ
ከፍ ፡ ካሉት ፡ በላይ ፡ እጅግ ፡ ከፍ ፡ ብለህ
ድካምና ፡ ዝለት ፡ ሳያውቅህ ፡ እርጅና
ትናንትና ፡ ዛሬም ፡ ሁልጊዜ ፡ ገናና

ንጉሥ ፡ በንግሥናው ፡ አዋቂው ፡ በዕውቀቱ
ሊመስልህ ፡ ሲሞክር ፡ ሲጥር ፡ አይ ፡ ሰው ፡ ከንቱ
ነገር ፡ ግን ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሁሉን ፡ ሲያስተያይ
ሁሉን ፡ ብሎ ፡ ያልፋል ፡ የለህም ፡ መሳይ ፡ ሃሌሉያ

የለህም ፡ መሳይ (፫x) ፡ በምድር ፡ በሰማይ
የለህም ፡ እኩያ (፫x) ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ

እግዚአብሔር ፡ እንዲህ ፡ ይህን ፡ ይመስላል
ተብሎ ፡ በቃላት ፡ መች ፡ ይገለጻል
አንዲያ ፡ ልጁ ፡ በቀኙ ፡ ያለው
ተረከው ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ማን ፡ አየው

ሰማይ ፡ ተቀምጦ ፡ እግሮቹ ፡ ምድር
ታላቅነቱ ፡ እንዴት ፡ ይነገር
መግለጫ ፡ ቋንቋ ፡ ቢጠፋም ፡ ቃሉ
እንዲሁ ፡ ብቻ ፡ ተመሥገን ፡ በሉ

የቱ ፡ ተነግሮ ፡ የቱ ፡ ይተዋል
የጌታ ፡ ዝና ፡ እጅጉን ፡ በዝቷል
ከየት ፡ አንስቼ ፡ ስንቱን ፡ ላስታውስ
በየማለዳ ፡ ሁልጊዜ ፡ አዲስ

የለህም ፡ መሳይ (፫x) ፡ በምድር ፡ በሰማይ
የለህም ፡ እኩያ (፫x) ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ (፪x)