ሽሽ ፡ እንጂ (Shesh Enji) - አዜብ ፡ ኃይሉ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
አዜብ ፡ ኃይሉ
(Azeb Hailu)

Lyrics.jpg


(2)

አሸናፊ ፡ ነኝ
(Ashenafi Negn)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2004)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:27
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የአዜብ ፡ ኃይሉ ፡ አልበሞች
(Albums by Azeb Hailu)

እያሳሳቀ ፡ ይወስዳል ፡ ውኃ
ወደ ፡ ሙት ፡ አገር ፡ ወደ ፡ በረሃ
እዳር ፡ ዳር ፡ ማለት ፡ በኃጥያት ፡ ሰፈር
ወድቆ ፡ ለማንባት ፡ ለመሰባበር

ሽሽ ፡ እንጂ ፡ ማነው ፡ ያለህ ፡ ተጠጋ
በጠላትህ ፡ ቀስት ፡ እንዳትወጋ
ኃጢአት ፡ አይምርም ፡ አንተን ፡ አግኝቶ
የሚሻለው ፡ ግን ፡ ማምለጥ ፡ ነው ፡ ሸሽቶ

ይቅርብህ ፡ እንዲያው ፡ በዋል ፡ ፈሰስ
ይቅርብህ ፡ በሕይወት/በነፍስ ፡ ላይ ፡ አመፅ
ይቅርብህ ፡ እንዲያው ፡ ወጣ ፡ ገባ
ዕድሜህን ፡ አታድርገው ፡ የእንባ (፪x)

ቅጥርን ፡ የሚያፈርስ ፡ እንደሚነደፍ
ከፅድቅ ፡ ክሌ ፡ አትውጣ ፡ አትለፍ
እንደ ፡ ተራበ ፡ ሆኖ ፡ እንደ ፡ አንበሳ
ይጠብቅሃል ፡ ክፉ ፡ እያገሳ

ፈቀቅ ፡ ብትል ፡ አንዲት ፡ እርምጃ
መመለስህን ፡ መምጣትህን ፡ እንጃ
የተከፈተው ፡ የአውሬው ፡ መንጋጋ
ውጦ ፡ ያስቀርሃል ፡ አትዘናጋ

መለስ ፡ እስኪ ፡ አንዴ ፡ በል ፡ መለስ
አስብ ፡ በእርጋታ
አይሻልም ፡ ዎይ ፡ መኖር ፡ በጌታ

የሚያስጐመጀው ፡ ሁሉ ፡ አይበላ
ሞትን ፡ ደብቆ ፡ ይዟል ፡ ከኋላ
አትንካ ፡ ካለህ ፡ ቅዱስ ፡ አምላክህ
ስለሚያውቅ ፡ ነው ፡ አስተውል ፡ ባክህ

እሳትን ፡ እሳት ፡ አቅፎ ፡ በጉያው
በአንዲት ፡ ሌሊት ፡ ነዶ ፡ ይጋያል
ኃጢአት ፡ አድብቶ ፡ ቆሟል ፡ በደጅህ
እባክህ ፡ አትተኛ ፡ ነቃ ፡ በል ፡ እንጂ

ይቅርብህ ፡ እንዲያው ፡ በዋል ፡ ፈሰስ
ይቅርብህ ፡ በሕይወት/በነፍስ ፡ ላይ ፡ አመፅ
ይቅርብህ ፡ እንዲያው ፡ ወጣ ፡ ገባ
ዕድሜህን ፡ አታድርገው ፡ የእንባ (፪x)

ይቅርብህ (፫x)